ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በኮሮና በመያዛቸው ተጠባቂውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ አይዳኙም !

የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በቀጣይ ቀናቶች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ይካሄዳሉ። በነዚህ በርካታ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያዊያን አርቢትሮች እንዲዳኙ ከወር በፊት በካፍ መመረጣቸው ይታወሳል።
ከዚህም ውስጥ የፊታችን ሐሙስ በጆሀንስበርግ በኤፍኤንቢ ስታዲየም የደቡብ አፍሪካዎቹ ባፋና ባፋና ከጋናዎቹ ጥቋቁር ክዋክብት ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ  ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንዲመሩት አስቀድሞ ቢገለፅም አሁን በኮሮና ምክንያት በጨዋታው የሚዳኙት የኢትዮጵያ ዳኞች ቁጥሩ እንዲቀንስ ሆኗል።
ለኢትዮ ኪክ በደረሰን መረጃ መሠረት ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ ጨዋታውን ለመምራት ከአንድ ረዳት ዳኛ ጋር ወደ ስፍራው አቅንተዋል።
በአንፃሩ ይህን ጨዋታ ለመዳኘት ቀደም ብሎ አራቱም ኢትዮጵያዊያን አርቢትሮች የተመረጡ ቢሆንም አሁን በኮሮና በመያዛቸው ምክንያት ከአራቱ ሁለቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሳይጓዙ ቀርተዋል። በደረሰን መረጃ በኮሮና ምክንያት ከቀሩት ሁለቱ ዳኞች አንደኛው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የኮሮና ምርመራ ሰጥቶ ዕረቡ ኢትዮጵያ ከማላዊ ጨዋታን መዳኘቱም ለማወቅ ተችሏል።

One thought on “ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በኮሮና በመያዛቸው ተጠባቂውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ አይዳኙም !

Comments are closed.