በወንዶች አትሌት ሲሳይ የቦታውን ክብረወሰን ሰብሯል!
ከወሊድ መልስ አትሌት ወርቅነሽ ዳግም ወርቁን አጥልቃለች !
በ2023 የአለም የማራቶን ውድድር አንዱ የሆነው የቫሌንሺያ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቋል። ኢትዮጵያዊው ሲሳይ ለማ በወንዶች ገና ከጅምሩ ጠንከር ያለ ፍጥነት በመሮጥ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዳዊት ወልዴ እና ኬኒያዊው ኪቢወት ካንዲ ጋር መሪነቱን ቢቀላቀልም ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በመምጣት ውድድሩን በ 2፡01 48.በሆነ ድንቅ ሰአት የፍጻሜውን መስመር በማለፍ ባለፈው አመት በኬልቪን ኪፕተም (2:01:52) የተያዘውን የቦታውን ክብረወሰን ሰብሯል። አትሌት ዳዊት ወልዴ በ2:03:48 ሦስተኛኛ ሲሆን የአለም ሻምፒዮናው ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል።
በተመሳሳይ ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ከወሊድ መልስ በቫሌንሲያ ማራቶን 2፡15.51 ሰአት በሚያስገርም ሁኔታ አሸንፋለች፡ ወርቅነሽ በሴቶች የግል ምርጥ ሰዓቷን በታሪክ 7ኛዋ ፈጣን አትሌት ሆናለች። በዚሁ ውድድር አትሌት አልማዝ አያና የራሷን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባ 2ኛ ህይወት ገብረኪዳን 3ኛ ሆነው አሸንፈዋል::