ዜናዎች

-ኢትዮዽያ የምትካፈልበት የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የድልድሉ ቀን ተራዘመ ! – የአፍሪካ ዋንጫ ሊራዘም ይችላል ?

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዕጣ ማውጣት ድልድል ቀኑን ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑን አስታውቋል ፡፡
ካፍ ቀደም ብሎ የእጣ ማውጣት ቀኑን June 25 ከሶስት ሳምንት በኃላ እንደሚያካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ቀኑን ላልተወሰነ ጊዜ ያራዘመ መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ካፍ አዲሱ የእጣ ማውጣት ቀኑን በቅርቡ ይፋ የሚይደርግም ይሆናል ፡፡
ዋልያዎቹ ከስምንት ዓመት በኃላ ተካፋይ በሚሆኑበት የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንጆቹ 2021 በዚህ ዓመት ይደረጋል ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ባለው መረጃ ካፍ ምናልባትም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ ወደ ቀጣይ ዓመት ሊያዘዋወር እንደሚችል መረጃዎች ጠንክረዋል።