አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በቀናት ልዪነት ሌላኛውን ድል ደግማለች !

ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ላቪስ በተደረገው የ1500 ሜትር የቤትውስጥ ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት በገንዘቤ ዲባባ ለ7አመት ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ የሰበረችው ጀግናዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዛሬ ደግሞ በ 800 ሜትር በቁጥሬ ዱለቻ እ.ኤ.አ 1999 ተይዞ የነበረውን የ800ሜትር 1 :59.17 በማሻሻል 1: 57.52 አዲስ የአለም ፈጣኑን ሰአት አስመዝግባለች።