አትሌቲክስ ዜናዎች

-አትሌት ሲፋን ሀሰን ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፋች !

አትሌት ሲፋን ሀሰን እና  አትሌት ለተሰንበት ግደይ
በሄንግሎ -ኔዘርላንድ ትላንት ምሽቱን መላውን ኢትዮጵያዊያንን ያስደሰተ ድንቅ የ10ሺ ሜትር ክብረወሰን ላስመዘገበችው ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሪከርዱን በ48 ሰአታት የተነጠቀችው በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊት አትሌት ሲፋን ሀሰን የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፋች። አትሌት  ሲፋን ሀሰን የዓለም ክብረወሰኗን በመነጠቋ እንኳን ደስተኛ መሆኗን የሚከተለውን  ለኔዘርላንድ ኒውስላይፍ ድረ ገፅ ተናገረች
” በእንደዚህ በጣም በተቀራረበ የቀናት ልዩነት ሁለት የዓለም ሪከርድ መሠበር ማለት የ10 ሺ ሜትር ውድድር ምንያህል ተወዳጅ ርቀት መሆኑን የሚያመላከተ ነው። እንደዚህ አስደሳች ውድድሮችን ሰዎች እንዲዩ ከመነገር ውጭ ሌላ የምለው አይኖርም ” ካለች በኃላ አትሌቷ ቀጥላ
” ለዚህ ግሩም ስኬት ለተሰንበት ግደይ በመብቃቷ እንኳን ደስ ያለሽ እላለሁ። ትልቅ ስኬት ነው። ይህንን ስኬት እንደምታደርግ አውቅ ነበር። ስለሆነም በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ ያለሽ ማለት እፈልጋለሁ ፡፡ በመጣችው ውጤት በጣም ደስተኛ ነኝ። ለተሰንበት ጥሩ አትሌት ናት። እሷ ችሎታ እንዳላት ይህንን እንደምታሳካው አውቃለሁ ። በቀጣይ በቶኪዮ አስደሳች ውድድር እናደርጋን ብዬ አስባለሁ ” በማለት በ48 ሰአታት ልዪነት ክብረወሰኑን የተነጠቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ተናግራለች።
እንደሚታወሰው የ10,000 ሜትር ክብረወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ለ5 ዓመታት ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።