ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

አሰልጣኝ ገብረመድህን የመጨረሻ ጨዋታቸውን ዛሬ አድርገዋል- ነገ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ይጀምራሉ!

– ሰኞ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ለመሆን በልዩ ዝግጅት ፊርማቸውን ያኖራሉ!
👇
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ምሽቱን መድኖች ከፋሲል ከነማ ጋር ያደርጉትን የመጨረሻ ጨዋታው በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። አሰልጣኙ የዋልያዎቹ ቀጣይ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ነገ ጉዟቸውን ወደ ሸገር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
መረጃዎች ለኢትዮ ኪክ እንዳመለከቱት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እሁድ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጊን በሚገጥመበት ጨዋታ ላይ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይገኛሉም ተብሏል። በንጋታው ሰኞ አሰልጣኙ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ለመሆን ከፌዴሬሽኑ ጋር የፊርማ ስነስርዓቱን የሚያከናውኑም ይሆናል።
በተጨማሪም የኢትዮ ኪክ ምንጮ እንደጠቆሙት የፊርማ ስነስርዓቱ እንደቀድሞ በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ሳይሆን ተለቅ ባለ ሆቴል እና ከፍ ባለ ስነስርዓትና ለማድረግ እንደታሰበ ተስምቷል።