፣በ20ኛው ሳምንት የመጨረሻው ጨዋታ የነበረው ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳህና በ1ለ 1 አቻ ውጤት አጠናቀዋል። በሀዲያ ሆሳዕና በኩል ፀጋሰው ድማሙ በጭንቅላት ድንቅ ጎል አስቆጥሯል ። ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
በተከታታይ ሁለት ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል። ከተከላካይ ወደ ጎል ማስቆጠር መምጣት የሚኖረው በራስ መተማመን?
” በራስ መተማመኔ ከፍ እያለ ነው የመጣው ። የመጀመሪያ ሁለት ሶስት ጨዋታዎች ነው እየተጫወትኩ ነው ያለሁት። አሰልጣኙ ተደጋጋሚ ዕድልም እየሰጠኝም ነው አምኖ። ይሄ ለእኔ ትልቅ መነሳት ነው ።
ወጣት ከመሆኑ አንፃር ቃሚ ተሰላፊ ከአይሳክ ኢሴንዴ ቦታ ላይ ትገባለህ ስትባል የተሰማው ስሜት ?
” በጣም ነው ደስ ያለኝ ። ከእሱ በጣም ብዙ የምወስዳቸው ልምዶች አሉ። ከእኔ በተሻለ ነበር መጀመሪያ አካባቢ ላይ አንዳንድ ጉዳቶች እና ቢጫ በነበረ ሰአት ነበር ዕድሉን የተጠቀምኩት ለዛ ነው አሳልፎ የሰጠኝ”
ጎሉ ባለፈውም ያስቆጠረው ተመሳሳይነት አለው ልምምድ ቦታ ከሄኖክ ጋር ስለመስራቱ ?
” አዎ ከሄኖክ ጋር በአንድ ላይ ነው የምንሰራው። እንደወንድሜ ብዙ ነገር ይመክረኛል።አንዳንዴ ወጣትነትም ሲይዝህ ለምን አልገባሁም የሚል ስሜትም ሲመጣ ይመክረኛል። የእሱም እገዛ ከፍተኛ ነበር።
ሁለት ጊዜ ያስቆጥረካቸውን ጎሎች ለማን ታበረክታለህ ?
“ለእናቴ (በፈገግታ)
“