ከእስራኤል ብሔራዊ ቡድን ይልቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቱን ከዚህ ቀደም በተደጋገሚ ለኢትዮ ኪክ የገለፀው እና በዘንድሮ የእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ሳልልህ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ከፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነ መልካም ውይይት ዛሬ በቴላቪቭ አደረጉ።
ለረጅም ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የትውልድ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቹን በብሔራዊ ቡድኑ የማካተት ስራዎች ለማስጀመር በኢትዮትዮያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል አሁን ከፍተኛ ፍላጎት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
በተለየም የፌዴሬሽኑ ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጀርመን የሚገኘውና ለበርካታ ጊዜያት የውጭ ተጨዋቾች በብሔራዊ ቡድኑ እንዲካተቱ በሙያው የስካውቲንግ ስራ ለመስራት ሁሌም ፍላጎቱ ከሆነው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑና የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ዴቪድ በሻህ ጋር በዚህ ሳምንት በZoom እንደሚወያዩ እና ቀጣይነት ያለውን ተግባራት እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል።