ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው -ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኃላ ቦድስሊጋውን ተሰናበተ !

Theodor Gebre Selassie

ከኢትዮጵያዊ ዶክተር ወላጅ አባቱ እና ከቼክ ወላጅ እናቱ በቼክ ሪፐብሊክ የተወለደው ቴዎዶር ገብረ ስላሴ ከዘጠነኛው ዓመት የብሬመን እና የቦንድስ ሊጋው ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ ከክለቡ መለያየቱ ተዘግቧል።

እ.ኤ.አ.በ 2012 ዓ.ም ወደ ጀርመኑ ቦንድስሊጋ ተዘዋውሮ በብሬመን የቦንድስሊጋው ስኬታማ ጊዜን ያሰለፈው ቴዎዶር በ23 ቁጥር መለያ በ271 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎችን ወይም ረጅም ዓመት ለዎርደር ብሬመን በመሰልፍ ከፔሩ ክላውዲዮ ፒዛሮ ቀጥሎ በቡንደስ ሊጋው የተሰለፈ ሁለተኛ ታሪካዊ የውጭ ተጨዋቾች መሆኑም ታውቋል።

የ 34 ዓመቱ ታሪካዊ የብሬመን ተከላካይ ቡድኑ ከቀናት በፊት በ Borussia Mönchengladbach 4 ለ 2 ሽንፈት እና ብሬመንን ከቦንድስ ሊጋዉ መውረድ ሊታደግ ባለመቻሉ ከክለቡ ተለያይቷል። ክለቡም ታሪካዊውን ተጨዋች በክብር ሸኝት አድርጎታል ።