ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 3ኛ ሳምንት በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ 22 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ማጣሪያ ምክንያት በሳምንቱ ያልተካሄደው ብቸኛው የባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ በተስተካካይ ጥቅምት 19 በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚካሄድ ይታወቃል። በሳምንቱ 35 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ የተገሰፁ ናቸው።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥቅምት 6/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በክለቦች ደረጃ አርባምንጭ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋች አቤል ማሞ ለብሶት የገባው ማሊያ ቁጥር ከተመዘገበው የተለየ በመሆኑ እንዲሁም የማሊያው ቁጥር ከተፈቀደው ቁጥር ውጪ/ከ1-50/ በመሆኑ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ በሁለቱም ጥፋቶች ክለቡ ብር 6000 ስድስት ሺህ/ እንዲከፍል ሲወሰን ሲዳማ ቡና ባደረገው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
የክለቡ ደጋፊዎች ….. የፋሴል ደጋፊ ሲሳደቡ በዋለው