ዜናዎች

በገንዘብ ችግር የሚገኘው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከመንግስት የ50 ሚልዮን ብር ድጋፍ ይጠብቃል!

በአልጄርያ አስተናጋጅነት ከጥር 5/2015 – ጥር 27/2015 ድረስ በሚካሄደውና የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ከሚሳተፉት 18 ሀገራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዱ እንደሆነ ይታወቃል።
በምድብ ሀ ከአስተናጋጇ አልጄርያ ፣ ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ የሚያደርገው ዝግጅት ከሊጉ መቋረጥ በኋላ ይጀምራል። በአንፃሩ በቻን ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ለ ብሔራዊ ቡድን ከገንዘብ ችግር ጋር በተያያዘ ራሱን ከውድድሩ ሊያገል ይችላል ቢባልም ለቅድመ ዝግጅት እና ከውድድሩ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ወጪዎች ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚያስፈልግ በሚል ከኢፌዲሪ መንግሥት የ50 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠይቋል።
ፌዴሬሽናየኑ ከመንግሥት ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን ለመጠቀም አጋር ተቋማትን በማፈላለግ የሚጠበቀው የፋይናንስ አቅም ላይ ለመድረስ ጥረት ላይ ይገኛል።