በ22ኛው ሳምንት የረፋድ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለት ጎሎችን መስፍን ታፈሰ አስቆጥሯል። ከቅርብ ዓመታት ውስጥ ድንቅ ብቃት እያሳየ የመጣው ወጣቱ የሐዋሳ አጥቂ መስፍን ታፈሰ ከሳምንት በፊት ከኢትዮኪክ ጋር ባደረገው ቆይታ የቤትኪንግ በቀጣይ ሐዋሳ ላይ መሆኑ ለቡድናችን ይጠቅማል በማለት አስተያየት መስጠቱ ይታወሳል። በዛሬው ጨዋታ ሁለት ጎሎች ያስቆጠረው መስፍን ታፈሰ ከጨዋታ በኋላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ስለጨዋታው ?
” አሪፍ ነበር( በፈገግታ) “
ሀዲያ ሆሳዕና በቁጥር ጎድለው 1 ለ 0 ለረጅም ሰዓታት መቆየታቸው ከጭንቀት አንፃር ?
” አዎ ያጋጥማል አንዳንዴ ኘየየእንደዚህ። እኛም በጣም ውስጣችን ጭንቀት ነበር ለማግባት ። ችኮላችን እንድንጓጓ አድርጎናል ማለት ነው”
ከጎል ርቆ በዛሬው ጨዋታ ማስቆጠሩ የሚሰጠው ትርጉም ?
” ለእኔ በጣም ደስ ብሎኛል። በዛሬው ጨዋታ በግዴታ ሶስት ጎል አገባለሁ ብዬ ነበር የመጣሁት። እናም ሁለት አግብቻለሁ። ብዙ ሞክሪያለሁ። አንደቀ ቀን ማሳካቴ አይቀርም ብዪ አስባለሁ”
እነሱ በመጉደላቸው ነው ሶስት አገባለሁ ያልከው?
” አይደለም። በራሴ ማለት ነው። ከጨዋታ ርቄ ነበር። በዛ ምክንያት ነው”
በሜዳ ውስጥ የነበረው ስሜት እንዴት ነበር ። እነሱ ተዘራ ሲወጣ 9 ነበሩና
” ያው እኛ ለማግባት ነው። ችግራችን ለማግባት መቸኮላችን ነበር ። ግን በቃ ለማሸነፍ ነበር አላማችን ቢሆንም ሶስት አግብተን ወጥተናል። ይመስገን ነው”
ሐዋሳ ላይ ነው ጨዋታው እስከምን መሄድ ነው የምት ፈልጉት ?
“ያው ዋንጫው እንደሆነ ተበልቷል (በፈገግታ) ያው እኛ ኮንፌዴሬሽን ለመሳተፍ ነው”
ጎልን መታሰቢያ ለማን ይሁን ?
” ለአባታ (በፈገግታ)”
ሲሆን ወጣቱ አጥቂ እንደሚታወሰው በፕሮፌሽናልነት የሙከራ ዕድል ባለፈው አመት ከወኪሉ አቶ ሳምሶን ነስሮ ጋር ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ተጉዞ ልምድ አግኝቶም ተመልሷል።
መስፍን ከቅርብ ሳምንታት በጉዳት መልስ በቤትኪንግ ላይ ያለተሰለፈ ይገኛል።