አፍሪካ ዜናዎች

#በነገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጎል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል። ሆኖም በአንጋፋው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በ 5፡00 ላይ የሚከናወን በመሆኑ የሰዓት መጣበብ እንዳይኖር በማሰብ ጋዜጣዊ መግለጫው በአንድ ሰዓት ተገፍቶ ከቀኑ 9፡00 እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።