በአሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚሰለጥነው ሰበታ ከተማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ከወራጅ ስጋት ተላቆ ነጥቡን በተሻለ ሆኖ ለማጠናቀቅ ዛሬን ጨምሮ ሶስት ጨዋታዎች ይቀሩታል። የቡድኑ የዘንድሮው ስብሰብ አንፃር ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የተጠበቀው ባይሆንም በሊጉ በመቆየቱ በቀጣይ የቡድኑን ችግሮች የሚፈትበት ጊዜ ይኖረዋል።
በአንፃሩ ክለቡ ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ከተጨዋቾች ጋር ችግሮቹን የሚፈታ ካልሆነ በርካታ ተጨዋቾች ከክለቡ ጋር ውላቸው ዘንድሮ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በሰበታ ከተማ መልካም እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከነበረው እና ከቡድኑ ጋር የውል ኮንትራቱ ዘንድሮ ከሚጠናቀቅው ፉሀድ ፈረጃ- ጋር ኢትዮ ኪክ ቆይታ አድርገናል።
ኢትዮኪክ :- የዘንድሮ የቡድናችሁ አቋም በአንተ እይታ እንዴት ነው ?
ፉሀድ :-;በእኔ እይታ ጥሩ ነበረን ብዬ አስባለሁ፣ ምክንያቱም የተመቸኝን የጨዋታ ፍልስፍና ተግባብተን እየተጫወትን ነው ብዬ አስባለሁ። እንደ መጀመሪያ አመት ጥሩ ነው ግን ያሰብነው ከዚህ በላይ ነበረ።
ኢትዮኪክ :- ዘንድሮ ፉሀድ አቋሙን እንዴት ያስቀምጠዋል?
ፉሀድ :- ሙሉውን ውድድር በጥሩ አቋም ለመጨረስ ነበር ሀሳቤ። ነገር ግን እግርኳስ ነውና ጉዳት ባላሰብኩት መንገድ ባያደርገኝም ግን በተጫወትኩበት ጨዋታዎች ምርጥ ብቃቴን ማሳየት ችያለሁ ብዬ አስብለሁ ግን ብዙ የሚቀረኝ ነገር እንዳለ ሆኖ ።
ኢትዮኪክ :- አንዳንዶች ፉሀድ በተወሰነ መልኩ ጥሩ ይሆንና በተወሰነ መልኩ ወጥ አቋም አይታይበትም ይላሉ ይሄ ከምን የመጣ ነው ?
ፉሀድ :- ያው እንዳልኩት ጉዳት ያመጣብኝ ተፅዕኖ ይመስለኛል ፣ የጉዳት መደራረቡ ባለኝ አቅም እንዳልቀጥል ያደርገኛል። አላህ ይመስገን አሁን ጥሩ ላይ ነኝ ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮኪክ :- ከደሞዝ ክፍያ ጋር የተነሳው ጥያቄ በወጥ አቋማችሁ ላይ ተፅኖው ይኖረዋል ?
ፉሀድ :- አዎ ያም ነገር ተፅዕኖ ያመጣው ብዬ አስባለሁ ።
ኢትዮኪክ :- ውልህ ዘንድሮ ያልቃል?
ፉሀድ :- አዎ ..ዘንድሮ ያልቃል።
ኢትዮኪክ :- ምንድነው በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ከቡድነህ ጋር የምታስበው?
ፉሀድ :- በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ላይ ለቡድኔ የምችለውን ለማድረግ እየሞከርኩ ነው ። ቡድኔ የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ በቀሪዎቹ ጨዋታዎች አሸንፎ የተሻለ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ነው ከአላህ ጋር ፍላጎቴ።