ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

በስዊድን ሊግ የሚጫወተው ቢኒያም በላይ በግል ጉዳይ ኢትዮዽያ ይገኛል !

ለስዊዲኑ ኡሚያ ኤፍ ሲ ክለብ የመስመር ተጨዋች የነበረው ኢትዮዽያዊው ቢኒያም በላይ በግል ጉዳይ በአሁን ሰአት በኢትዮጵያ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። በስዊዲን Superettan የክለቦች ውድድር ላይ ለክለቡ ኡሚያ ኤፍ ሲ ከኮሮና እረፍት መልስ ሊጉ ሲጀመር በተደጋጋሚ የጨዋታው ኮከብ በሚል ሽልማት ያገኘውና በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ የነበረው ቢኒያም በላይ በአሁኑ ሰአት በአገር ቤት እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል። የኡሚያ የመስመር ተጨዋች ቢኒያም ከክለቡ ጋር ስምምነቱ ያበቃ ሲሆን በጥሩ አቋም ላይ መሆኑን ተከትሎ ከቤልጅየም እና ከስዊድን ተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች ጥያቄ ቢያቀርቡለትም በግል ጉዳዮ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዮን መቆየት ተከትሎ ቀሪዎቹን ወራቶች ቢንያም በኢትዮጵያ እንደሚቆይም ታውቋል።መረጀዎች እንደሚጠቆሙት ከሆነ ቢኒያም በላይ ቀጣይ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር ላይ በአንዱ ጠንካራ ክለብ ውስጥ ተጨዋች ሆኖ እንደሚታይ ተገምቷል። እስካሁን ባለው መረጃ ቢኒያም በላይ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በየትኛው ክለብ ሊገባ እንደሚችል መረጃው አይገልጽም።