በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች አራት ጎሎች ያስቆጠረው እና ዛሬ ሲዳማ ቡና ተጋጣሚውን ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሁለቱንም ጎሎች ያስቆጠረው ይገዙ ቦጋለ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
በቅድሚያ እንኳን ደስ ያለህ
” እግዚአብሔር ይመስገነው”
የውድድር ዓመቱ በጉዳት በሀዘን አሁን ደግሞ ደስታ እንዴት ነው ስሜቱ ?
” ውድድሩ እንደተጀመረ ጥሩ አቋም ላይ ነበርኩ? ግን ጉዳት አጋጥሞኝ ነበር ከሜዳ የራቅኩት እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ጥሩ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው”
በጨዋታው ጎል አስቆጥራለሁ ብሎ አስቦ ስለመሆኑ?
” በርግጠኝነት እንደማስቆጥር አምኜ ነው የመጣሁት። ሶስት አገባለሁ ብዬ ነበር የመጣሁት ያው አልሆነም እግዚአብሔር ይመስገን። ሁለት አግብቻለሁ”
ሲዳማ ቡና ላለመውረድ ነበር በኃላ ግን አለመውረዱን ሲያረጋግጥ የቡድኑ ስሜት ?
” አዎ መጀመሪያ ልክ ነው ላለመውረድ ነበረ እየተጫወትን የነበረው። ከድሬዳዋ ቆይታ ጀምሮ ቡድኑ ተነጋግሮ ሁላችንም አሰልጣኞችም ቡድኑ እንዳይወርድ በሚል መለወጥ የጀመርነው”
ከወራቶች በፊት በጉዳት አልቅስ ከሜዳ ወጥቶ ነበረ፣ ከዛ በኃላ በስነልቦና ጠንክረህ እንድትመጣ የረዳህ ምንድነው ?
” ፀሎት ነው የረዳኝ”
ለሌሎቹ የምትመክራቸው ?
” በቃ ፈጣን ነው “
Bravo man