ዜናዎች

“በሜዳ ላይ ብቃት በቡድናችን ደስተኛ ነኝ፣ ጥሩ ክመጫወታችን አንፃር ሰባተኛ ነን ማለት አንችልም ” – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሐምሌ 10/2013 የተጀመረው እና የፊታችን ዓርብ የፍፃሜ በሚሆነው  የምስራቅ እና መካከለኛው ከ23 ዓመት በታች  የዋንጫ ውድድር የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች በደከመ እንቅስቃሴ ውድድሩን በ7ኛ ደረጃ አጠናቋል።
በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን ከቀረቡት 9 ቡድኖች እጂጉን ደካማ ነበር ማለት ይቻላል። እንደሚታወሰው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ለውድድሩ ሶስት የወዳጅነት ጫዋታ አድርጎ ነበር። በአንፃሩ ሶስቱንም ከከፍተኛ ዲቪዚዮን ቡድኖች ጋር  እንደነበር ይታወሳል። ይሁንና ቡድኑ ካደረገው የወዳጅነት  አንፃር  በትክክል አቀሙን ፈትሾ ነበር ለማለት ይከብዳል። 
 በአጠቃላይ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ያመጣው ውጤት ሻምፒዮናውን ዝቅ ባለ ግምት ሰጥቶት የተወዳደረው አስመስሎታል። ያገኘው ውጤት ለውድድሩ ከተዘጋጀበት አንፃር ነው ማለት ይቻላል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዛሬውን ጨዋታ አና አጠቃላይ በሻምፒዮናው አስመልከተው ከተናሩት መሃል “በደረጃ 7ተኛ እና ስምንተኛ የሚኖርበት ቢሆንም በሜዳ ላይ ብቃት ግን በቡድናችን ደስተኛ ነኝ፣ ከቡድናችን ጥሩ  ክመጫወታችን አንፃርም ሰባተኛ ነን ማለት አንችልም'” ብለዋል
እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ ቡድኑ በሻምፒዮናው ያደረገው እንቅስቃሴ እጅግ የወረደ ነበር ማለት ይቻላል። በአንፃሩ በውድድሩ በቀጣይ ለሚኖረው የአፍሪካ ዋንጫ የተከሰቱ ስህተቶች ለማየት ይጠቅማልና ባለሙያዎቹ አስቀድመው እንደ ሌሎች አገራት አማራጮችንም አፅኖት ቢሰጡበት መልካም ነው።