አፍሪካ ዜናዎች

በልምምድ ሜዳ ህይወቱ በድንገት ያለፈው የአማካይ ቦታ ተጨዋች !

የጊኒ እግር ኳስ ዛሬ በሀዘን ውስጥ ይገኛል። ለጊኒ የዋናው ሊግ HAFIA FC ክለብ በአማካይ ቦታ ተጨዋች የነበረው ወጣት ሞሀመድ ላቲጌ ካማራ የተባለው ተጨዋች በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።የ24 አመቱ ተጨዋች ሞሃመድ ላቲጌ ህይወት በድንገት ያለፈው ዛሬ ረፋድ በኖንጎ ከቡድን ጓደኞቹ ጋር መደበኛ ልምምድ እየሰሩ ሳለ ድንገት ጥሩ ያልሆነ ስሜት ተሰምቶት ብዙም ሳይቆይ ራሱን ስቶ ሲወድቅ የቡድን አጋሮቹ በአስቸኳይ በጊኒ ቻይና ሆስፒታል ይዘውት ቢደርሱም ህይወቱ ሳይትርፉ የወጣቱ ተጨዋች ህይወቱ አልፏል።  የቀድሞው የፌሎ ስታር አምበልየ24 አመቱ ወጣት ሞሃመድ ላቲጌ እ.ኤ.አ 2020 የጊኒ የቻን ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ተጫውቷል።

 

One thought on “በልምምድ ሜዳ ህይወቱ በድንገት ያለፈው የአማካይ ቦታ ተጨዋች !

Comments are closed.