ዜናዎች

-ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ የውጭ አሰልጣኝ ቀጠረ ! . የአሰልጣኙን ማንነት ከመግለፅ ተቆጥቧል !

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ዛሬ ለስፖርት ማህበሩ የሚዲያ ክፍል በሰጡት መግለጫ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚመጥን አዲስ የአሰልጣኝ ቅጥር ተከናውኗል ብለዋል፡፡ አዲሱ አሰልጣኝ በአፍሪካ ታዋቂ ክለቦችን ያሰለጠነና በተለይም እንደ ቲፒ ማዜምቤ አይነት ክለቦችን በማሰልጠን ውጤታማ የሆነ ነው ብለዋል፡፡ይሁንና ክለቡ የአሰልጣኙን ስም እና ማንነት ያፋ ባያደርግም አሰልጣኙ ከቅድመ ዝግጅት በፊት ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡም ክለቡ አስታውቋል ፡፡