ዜናዎች

ሽመልስ በቀለ ለሌላኛው የግብጽ ክለብ ፊርማውን አኖረ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይና በግብፅ ሊግ የተሳካ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ከግብፁ ክለብ ምስር ኤል መቃሳ ጋር በመለያየት ለሌላኛው የግብፅ ክለብ ኤል ጎውናን ለቀጣይ ዓመት ለመጫወት ፊርማውን ብሔራዊ ቡድኑን ከመቀላቀሉ በፊት አኑሯል ።
በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ አመታት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ዘንድሮ በ 11 ጎሎች አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ሽመልስ በቀለ በቀጣይም ዓመት በሌላኛው የግብፅ ክለብ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን ይቀጥላል። የዋልያዎቹ ሁለተኛ አምበል ሽመልስ በቀለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር በሚያደርገው በምሽቱ ጨዋታ የሚሰለፈም ይሆናል ።
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያዊ  ጋቶች ፓኖም ከዚህ ቀደም በኤል ጎውና ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል።