ዜናዎች

ሽመልስ በቀለ 8ኛ ጎሉን አስቆጥሮ – ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎቹ አንዱ መሆኑን ቀጥሏል!

ሽመልስ በቀለ - ምስር ኤል ማካሳ
ሽመልስ በቀለ – ምስር ኤል ማካሳ
ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ በግብፅ ፕሪምየር ጎል ማስቆጠሩን ቀጥሏል።ከቀናት በፊት ብቸኛውን ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስቻለው ሽመልስ በምሽቱ ጨዋታ ቀዳሚውን ጎል በ7ኛው ደቂቃ ለክለቡ አስቆጥሯል።
የግብፅ ፕሪምየር ሊግ በ22ኛው ሳምንት ጨዋታ የቀድሞ የኡመድ ኡክሪ ክለብ የነበረውን አስዋንን የገጠመው የሽመልስ ክለብ ምስር ኤል ማካሳ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን  ከ8ኛ ወደ 5ኛ ደረጃ ማሻሻል ችሏል።
በዘንድሮው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ በ11 ጎል በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ከሚመሩት ሁለት ተጨዋቾች በተጨማሪም በ10 ጎሎች እና በ9ጎሎች ከሚመሩት  በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ጋር ሽመልስ በቀለም በ8 ጎሎች በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ሰንጠረዥ አራተኛ ላይ ተቀምጧል።