ዜናዎች

ሱራፌል በአሜሪካው ሎውዶን ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ ያደርጋል!

👇
ኢትዮጵያዊው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸው በአሜሪካኑ የዋናው ሜጀር ሊግ (MSL) ተወዳዳሪ ለሆነው ለዲሲ ዮናይት መጋቢ ክለብ በሎውዶን ዩናይትድ ለመጫወት የሚያስችለውን የሊጉ እና የፌደራል ፈቃዶችን በማጠናቀቁ ክለቡ ከነገ በስቲያ በሚያደርገው USL( United Soccer Legaue) ጨዋታ ለአዲሱ ክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚሰለፍ ይሆናል.
ሱራፌል ዳኛቸው በአዲሱ ክለቡ በሎውዶን ዩናይትድ 19 ቁጥር ማሊያ የሚለብስ ሲሆን ከቡድኑ ጋር ዛሬ ልምምድ ሰርቷል.
ኢትዮጵያዊው ሱራፌል ዳኛቸው እስካሁን በሎውዶን ዩናይትድ ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን አድርጎ በሁለቱም ጨዋታዎች አምበል የነበር ሲሆን ጎልም አስቆጥሯል.
የሊጉ እና የፌደራል ፈቃዶችን ያጠናቀቀው ሱራፌል በቨርጂኒያ ሊዝበርግ ከተማ የመኖሪያ ቤት እና መኪናም በክለቡ የተሟላለት ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥም ቤተሰቦቹ እንደሚመጡ ታውቋል!