ዜናዎች

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከዋልያዎቹ ጋር በመሆን  በአልማዝዬ ሜዳ የትጥቅ ድጋፍ አደረጉ !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከክፍለ ከተማ በሚገኘው ቄራ አልማዝዬ ሜዳ ዛሬ ረፋድ በመገኘት  ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በመሆን  ለቄራ አንበሳ ስፖርት ማህበር የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ።   በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቄራ እና አካባቢው የሚኖሩ ባለሀብቶች በበኩላቸው የአልማዝዬ ሜዳን ከዲዛይን ጥናት ጀምሮ ሙሉ የሜዳውን ግንባታ ለማካሄድ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ለመቆም ቃል ገብተዋል ።  በርካታ ስፖርተኞችን ያፈራው አልማዝዬ ሜዳ  መሆኑን የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ በዘመናዊ መንገድ ግንባታው ይካሄዳል ብለዋል ።  የትጥቅ ድጋፍ ዝግጅት ላይ  ክከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ  እና ዋልያዎቹ በተጨማሪም  የተለያዩ ባለሀብቶች እና አርቲስቶች ተገኝተ ዋል  ።
 ፎቶ ክአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት