ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጀሪያ ሊያመራ ነው ! ጌታነህ ወደ ፋሲል ከነማ?

የ2013 ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ከጎል አዳኛቸው ሊለያዪ  ሙጂብ ቃሲም  ወደ አልጄሪያው  Jeunesse Sportive de Kabylie Fc (JSK) ሊያመራ መሆኑ ተሰምቷል ። 
ኢትዮኪክ ጉዳዮን ከሰማንበት ጊዜም ጀምሮ ስለጉዳዩ ሙጂብ ቃሲምን ጠይቀን ምላሹን እየጠበቅን ሲሆን  ሙጂብን እንዳገኘነው ምላሹን የምናሠማ ይሆናል። እንደ መረጃው  ከሆነ ግን የሙጂብ የአልጄሪያው ዝውውር መሣካቱ ተሰምቷል።  በተጨማሪም የፋሲል ከነማ አመራሮች ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ለሙጂብ መሸኛ ሊሰጡት መሆኑ ተሰምቷል። በተያያዘ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በስምምነት የተለያየውን ጌታነህ ከበደ ሊያስፈርሙ መሆኑ ተሰምቷል።
ሙጂብ ቃሲም

One thought on “ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጀሪያ ሊያመራ ነው ! ጌታነህ ወደ ፋሲል ከነማ?

Comments are closed.