ዜናዎች

ሉሲዎቹ በአጠቃላይ 14 ለ 0 አሸንፈዋል !

ሉሲዎቹ ከ የደቡብ ሱዳን ጋር ዛሬ ያደረጉን የወዳጅነት ጨዋታቸውን 3 ለ 0  አሸንፈዋል ።እንደሚታወሰው ከቀናት በፊት ሉሲዎቹ 11 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአጠቃላይ 14 ለ0 አሸንፏል ። በዛሬው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በ26ኛው ደቂቃ ሴናፍ ዋቁማ አስቆጥራ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።ከእረፍት መልስ ሴናፍ ሁለተኛውኝ በድጋሚ በ51ኛው ደቂቃ አስቆጥራለች። ጨዋታው ሊጠናቀቅ በ87ኛው ደቂቃ አረጋሽ ካልሳ ሶስተኛውን ጎል በማስቆጠር ደቡብ ሱዳንን አሸንፈዋል።