አትሌቲክስ ዜናዎች

ለተሰንበት ግደይ የ10,000 ሜትር ክብረወሰንን አስመለሰች !

አትሌት ለተሰንበት ግደይ

 

በኔዘርላንድ ሄንጌሎ ምሽቱን በተደረገ የ10ሺ ሜትር የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድር ላይ ከሁለት ቀናት በፊት በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊት በሆነችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ተሻሽሎ የነበረው እና ላለፉት 5 ዓመታት በአትሌት አልማዝ አያና ተያይዞ የነበረውን ሪከርድ በሁለት ቀናት ልዩነት በምሽቱ ውድድር ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።
ከቀናት በፊት አትሌት ሲፋን ሀሰን ተሻሽሎ የነበረው 29:06.82 ክብረወሰን በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ርቀቱን በ 29:01:03 በማሻሻል ክብረወሰኑን ወደ ኢትዮጵያ አስመልሳለች።