ዜናዎች

ሀዲያ ሆሳዕናንሙሉጌታ ምህረትን አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ ! – ለሁለት ዓመት ፈርሟል

በ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር በጠንካራ ተፎካካሪነት የውድድር ዓመቱን በአራተኝነት ያጠናቀቀው ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የውል ስምምነታቸው ከማጠናቀቃቸው በፊት አሰናብቶ ዶክተር እያሱ መርሐፅድቅ አሰልጣኝ አድርጎ የውድድር ዓመቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።  ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ ከክፍያ ጋር በተያያዘ በርካታ ተጨዋቾችን ከአሰልጣኝ አሸናፊ መሠናበት  ጋር ማጣቱም አይዘነጋም።  ሆኖም  ክለቡ የታዳጊ ቡድኑን ተጨዋቾች ወደ ዋናው በማዘዋወር  የውድድር ዓመቱን በጥሩ ተፎካካሪነት አጠናቋል።
አሁን ደግሞ ሀዲያ ሆሳዕና  በ2014 ዓ.ም በአዲስ አሰልጣኝ ለመቅረብ አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ የሐዋሳ ከተማውን ሙሉጌታ ምህረትን መሾሙ ታውቋል ። ሙሉጌታ ምህረት ከሃዲያ ሆሳዕና  ክለብ  ጋር   አሰልጣኝ ሆኖ ለመስራት  የሁለት ዓመት ስምምነትም ማድረጋቸው ተዘግቧል።