ዜናዎች

UMBRO ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የስፖንሰር ውሉን ለአራት ዓመት አራዘመ !

የኢትዮዽያ የወንዶች እና የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የትጥቅ ቴክኒካል ስፖንሰር የሆነው የደቡብ አፍሪካው ግዙፍ የትጥቅ አምራች ኩባኒያ ኡምብሮ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ህጋዊ ስፖንሰር በመሆን ውሉን ማራዘሙን በመግለጫ አሳውቋል።እ.ኤ.አ ከ 2019 ጀምሮ የኢትዮዽያ የወንዶች እና የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ስፖንሰር ለመሆን ውሉን ተስማምቶ የነበረው ኡምብሮ በቀጣይ አመታትም ቡድኑ በጨዋታ ሰዓት ፣ በልምምድ ሰዓት እንዲሁም ፣ አሰልጣኞቹ የቴክኒክ ክፍሉ አባላት በአጠቃላይ ከሜዳ ውጭ ልዑካን ቡድኑ የሚለሰውን ጨምሮ ትጥቆች በማቅረብ የስፖንሰርሺፕ አድራጊነቱን በአዲሱ ስምምነት ማራዘሙን በመገልጫ አሳውቋል።
ኡምብሮ በአሁኑ ሰአት በአለም ዙሪያ ከ150 ቡድኖች ትጥቆችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ኡምብሮ በእግር ኳስ ስፖርት የምርቶቹን በአፍሪካ ውስጥ 9 ፌዴሬሽኖች እና በመላው አህጉሪቱ ደግም 34 ፕሮፌሽናል ክለቦች ስፖንሰር በማድረግ ቀዳሚ ነው።።