የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አስተናጋጅ የድሬዳዋ ከተማ ከ17ኛ ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት የሚካሄደውን ውድድር ዛሬ ጀምራለች። በሞቃታማዋ ድሬ ዛሬ በተጀመረው እና በታሪካዊው የድሬጀዋ ስታዲየም በተካሄደው የ10:00 ሰዓቱ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ ያለ ጎል 0 ለ 0 ተለያይተዋል። ይህ ጨዋታ በDSTV የተላለፈ ቢሆንም በአንፃሩ ምሸት በ1:00 ሰዓት የተካሄደው የኢትዮጵያ ቡና እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በDSTV አልተላለፍም።
ጨዋታው በቀጥታ ስርጭት ያስተላለፈበት ምክንያት ቀደም ብሎ እንደገለፀው በስቴዲየሙ ዙሪያ የተገጠሙት የመብራት ፓውዛዎች ጨዋታውን በቀጥታ ስርጭት ለማከናወን በቂ ባለመሆነቸውና የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ቀረፃ የሚጠበቀውን የቀረፃ የደረጃን ጥራት ባለሟሟላታችው ነበር።
ለኢትዮ ኪክ ምሽቱን በደረሰን ሰበር ዜና የተከሰተው ችግር እንዲቀረፍ እና DSTV በቀጣይ ስታዲየሙ የማታ ጨዋታዎችን በተባለው ጥራት እንዲያስተላልፍ የናሽናል ሲሚንት አክሲዮን ማህበር ባለቤት ዶክተር ብዙአየሁ ታደለ በ2.4 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ለችግሩ በአፋጣኝ ምላሽ ሰጥተዋል ።
የተሰጠው LED መብራቶች እና የስታዲየሙ መብራት የከፍተኛ ኅይል ተሸካሚ ትራንስፎርመር ተከላ የድሬዳዋ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ምሽቱን ያደረገ ሲሆን የመስመር ዝርጋታና የባውዛ ተከላው ተጠናቋል።በደረሰን መረጃ መሠረትም ታሪካዊው የድሬዳዋ ከተማ ስታዲየም ሌላ ችግር ካላጋጠመው በስተቀር በቀጣይ በምሽት የሚደረጉን የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በሱፐርስፖርት በጥራት በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፍ ይሆናል። የነገ ምሽቱም ተጠባባቂው ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ ጨዋታ የቀጥታ ሽፋን በDSTV ይኖረዋል ሲሉ ምንጮቻችን ከስፍራው አድርሰውናል። ።