ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ከ14ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን መካሄጃ ከተማና ስታዲየም በተመለከተ የስራ አመራር ቦርዱ ዛሬ ጥር 28/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ውድድሩን በድሬደዋ ወይም ባህር ዳር ከተማ ለማከናወን የፊታችን ሰኞ ጥር 29/2015 ዓ.ም ሜዳዎቹን የሚገመግም ኮሚቴ(ከቦርዱ እና ውድድርና ስነስርዓት […]
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ
#ሰለ ነገው ሸገር ደርቢ / 2015 ተጨማሪ መረጃዎች
የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም * ትኬት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መሸጥ ይጀምራል። * የስታዲየም በሮች በተመሳሳይ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ። * የክቡር ትሪቡን በር በተዘጋጁ ልዩ ባጆች ብቻ የሚገባበት ሲሆን ጥላ ፎቅ 200 ብር ፣ ከማን አንሼ 100 […]
ለ45ኛ ጊዜ ሳንጃው ከ ቡንዬ የሚያደርጉት ስደተኛው ሸገር ደርቢ በቀዘቀዘ መልኩ ነገ ይካሄል !
ቀደም ባሉት አመታት ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በሚኖሩ ሳምንታቶች ብሎም ቀናቶች ጀምሮ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ደምቆ በጨዋታው ቀን ደግሞ ምሽት ለሚደረግ ጨዋታ ከሌሊት ጀምሮ ቦታ ለማግኘት ወረፋ የሚያዝለት እና የአዲስ አበባ ስታዲየም በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በተገኘው መድረክ ሲበዛ የሚደምቀው ሸገር ደርቢ ዘንድሮም በቀዘቀዘ መልኩ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ የፊታችን ቅዳሜ […]
#ፈረሰኞቹ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልምምድ ስፍራና ሆስቴል ግንባታ መሬት ባለቤትነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተረከቡ!
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም በወሰነው ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የልምምድና የተጫዋቾች ማረፊያ ሆስቴል ግንባታ ቦታ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፤ በመሆኑም ክለቡ አስፈላጊውን የሊዝ ውል በመፈፀም እና ለይዞታውም በ20/05/2012 ዓ.ም. ካርታ በማግኘት ጭምር ቦታውን ለማልማት የተለያዩ ጥረቶች ያደረገ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት ቆይቷል። በተለይም በይዞታው ላይ 3 የይገባኛል ክሶች ቀረበው ከሁለት ዓመታት […]
#የሸገር ደርቢን እና በታላቁ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት አስመልክቶ ፈረሰኞቹ የቀን ለውጡን ዛሬ ይፋ አድርገዋል!
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 87 ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ለማክበር ቀደም ብሎ ፕሮግራም መያዙ ይታወቃል። በአንፃሩ በርካታ ተጨዋቾችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ በድን ያስመረጡት ፈረሰኞቹ ተጫዋቹ በዚህ ሣምንት ከአልጄሪያ ይመለሳሉ በተባለው ቀን በትኬት ችግር አለመድረሳቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የሸገር ደርቢ በሳምንቱ መጨረሻ ያወጣው መርሐ ግብር ላይ ለውጥ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይ […]
#ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ ይቀጥላል! ሙሉ የውድድሩ መርሐ ግብር
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱ ይቀጥላል። በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የ12ኛ ሳምንቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 2015 ዓ.ም እንዲሁም የ11ኛ ሳምንቱ ወላይታ ድቻ ከሲዳማ ቡና እሁድ ጥር 21 […]
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 13ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 13ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አራት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 20 ጎሎች በ18 ተጫዋች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 36 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም። የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ታህሳስ 14 […]
#የፈረሰኞቹ የቀድሞ አሰልጣኝ ማሂር ውጤታማ አሰልጣኝ ፒትሶን ተከትለው ወደ ሳውዲ ሊግ አቅንተው !
የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው እና ለፈረሰኞቹን በ2013 ዋና ከረዳት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ቦታ ተሰጥቷቸው የነበሩት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ወደ ሳውዲ በማቅናት በአፍሪካ ውጤታማ አሰልጣኝ ለሆነው ሌላኛው የሀገራቸው ዜጋ አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ ምክትል አሰልጣኝ መሆናቸው ተዘግቧል። መረጃዎች ይፋ እንዳደረጉት የቅድስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ በሳውዲ አንደኛ ዲቪዚዮን አል አህሊ ስፖርት ክለብ አዲሱ ረዳት አሰልጣኝ […]
# በተጨዋቾች ላይ የሚከሰቱ ድንገተኛ የልብ አደጋዎችን ለመታደግ ነገ ስልጠና ይሰጣል!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ በአሜሪካ የልብ ማህበር በኢትዮጵያ አማካኝነት ለህክምና ባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው። ለአስራ ስድስቱ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የህክምና ባለሙያ እና ወጌሻዎች ለአንድ ቀን የሚሰጠው ስልጠና ባለሙያዎቹ ለውድድር በሚገኙበት ባህር ዳር ከተማ ይከናወናል። ቅዳሜ መስከረም 28/2015 ዓ.ም በሚካሄደው መርሃ ግብር በተለይም በእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የሚከሰቱ የልብና ተያያዥ ድንገተኛ አደጋዎችን መለየትና ማከም ላይ […]
ወደ ግብፅ ሊያመራ የተነገረለት አማኑኤል ከፈረሰኞቹ ጋር ውሉን አራዝሟል !
አጥቂው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር ተለያይቶ ወደ ግብፅ ሊግ ለመጫወት ከጫፍ ደርሷል ቢባልም ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያቆየውን የአንድ ዓመት ፊርማ ዛሬ አኑሯል ።