የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ የድሬደዋ ከተማ ከባህርዳር አቻው ጋር አንድ ለ አንድ ተለያይተዋል። ከጨዋታው በኃላ የድሬደዋው አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርገዋል። የሚገባውን ውጤት አግኝቷል ቡድንህ ? ጥሩ ነበርን። ባህርዳር ከነማ ያው ኳስን መስርቶ አድርጎ ነው ሚጫወተው። ግን ሜዳቸው ላይም ብዙ ይቆያሉ። ስለዚል እኛ በመልሶ ማጥቃት ጎል የማጎባት ዕድል ፈጥረን […]
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ
“ከጨዋታው ግለት አንፃር ውጤቱ ጥሩ ነው ” ምክትል አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን (ባህር ዳር ከተማ )
የ19ኛው ሳምንት የምሽቱ ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ከባህዳር አቻቸው ጋር ባደረጉት ጨዋታ አንድ እኩል አቻ አጠናቀዋል ። የባህርዳሩ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በጨዋታ አልተገኘም። የባህርዳር ከተማን በጨዋታው ይዞ የገባም ምክትል አሠልጣኙ ታደሰ ጥላሁን ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርገዋል። የሚፈልጉትን ውጤት ስለማግኘታቸው ? በተወሰነ መልኩ የምንፈልገውን አግኝተናል ማለት ይቻላል። ግን ይዘን […]
“ከቡድኑ ጋር ሶስተኛ ጨዋታዬ ነው ፣ዛሬ ለማሸነፍ ነበር አቻ ለመውጣት ሳይሆን ያንንም አሳክተነዋል። ” ➖ዑመድ ኡክሪ
እንደሚታወቀው ዑመድ በግብፅ ሊግ በአል ሂታድ አሌክሳንደርያ :፣ ኤን ፒ ፒ ፣ ኤል ኤታንግ ፣ ሶሞኦ እና አስዋን በመጫወት በቁጥር አምስት የሚደርሱ ክለቦች በመጫወት ቀዳሚ ያደርገዋል ። ዑመድ ኡክሪ ከግብፁ ሊግ የመጨረሻ ክለቡ አስዋን ወደ አገሩ ተመልሶ በሀዲያ ሆሳዕና እየተጫወተ ይገኛል።ከዛሬው ጨዋታ በኃላ ዑመድ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። ከግብፅ መልስ ሊጉን እንዴት አገኘኸው ? […]
“ግብ ጠባቂዎቹን ገልብጠን አጥቂ ቦታ ላይ አሰልፈናል ፤ እንደውም ተሳስተው ፔናልቲ ሳጥን በእጅ እንዳይዙ እያለን እየሰጋን ነበረ” – አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው
በቤትኪንግ የ19ኛው ሳምንት የትላንት ምሽቱ ጨዋታ ወላይታ ድቻ አንድም ተቀያሪ ተጨዋች ሳይኖረው በ11 ተጨዋቾች ብቻ ሃዋሳ ከተማ ገጥሞ ጨዋታን በ3 ለ 2 ተሸናፊነት አጠናቋል። ለችግሩ በዋነኝነት የኮቪድ ወረርሸኝ እና የተጨዋቾች ተደራራቢ ጨዋታ ለጉዳት በቀላሉ መጋለጥ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው። በትላንቱ የምሽት ጨዋታም የታየው ይኸው ነው። በወላይታ ድቻ በኩል በአጥቂ ቦታ ላይ ግብ ጠባቂዎቹ መክብብ እና አብነት […]
“ቅያሪ ተጨዋቾች ሳይኖርህ መጫወት እንደ አሰልጣኝ ያስጨንቃል ” -ሙሉጌታ ምህረት ( ሀዋሳ ከተማ)
የ19ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ምሽቱን በተካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች ስምንት ጎሎች ተቆጥረዋል። ከምሸት አንድ ሰአት ጀምሮ በተካሄደው የወላይታ ድቻ እና የሃዋሳ ከተማ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ 3 ለ 2 አሸንፎ ወጥቷዋል። በዚህ ጨዋታ ላይ ተቀያሪ ተጨዋቾች ያልነበሩት የመጀመሪያው የቤትኪንግ ጨዋታም ለመሆን በቅቷል። በሃዋሳ ከተማ በኩል አንድ ተቀያሪ በረኛ ብቻ ታይቷል።ከጨዋታው በኃላ የሐዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ሙሉጌታ […]
” ለእኔ የጨዋታው ምርጥ ማወሊ ነው፤ ሶስት ነጥብ ይዘን እንድንወጣ የቻለውን በእሱ በውጤት ነውና ” ➖ክሪዚሰቶን ንታንቢ ( ሰበታ ከተማ )
የሰበታ ከተማ ስፖርት ክለብ በ19ኛው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 አሸንፋዋል። የሰበታ ከተማ ቡድን የዛሬውን ጨወታ በማሸነፉም የደረጃ መሻሻል አድርገው በ7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሰበታ ከተማ በኩል የአማካኝ ክፍሉ በዛሬው ጨዋታ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ክሪዚሰቶን ንታንቢ ሲሆን ቡድንም ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሏል። የሰበታ ከተማው አማካይ ተጨዋች ክሪዚሰቶን ንታንቢ ከጨዋታው በኋላ […]
➖◾ የቤትኪንግ ሊግ – የድሬደዋ እውነታዎች ◾➖
የ18ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ በሦስት ቀናት ጨዋታዎች በአጠቃላይ 12 ጎሎች ተቆጥረዋል። የኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱ ሪከርድ ለመስበር የኢትዮዽያ ቡናው አቡበከር ናስር 22 አሰቆጥሮ ሶስት ጎሎች ቀርተውታል። በ18ኛው ሳምንት ፈጣኑ ጎል ሆኖ የተመዘገበው ሃዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር 1ለ1 አቻ በወጡበት ጨዋታ የጅማአባጅፋሩ ተመስገን ደረሰ ከእረፍት መልስ ፈጣኗ ጎል አስቆጥሯል። በ18ኛው ሳምንት ድንቅ ብቃቱን ያሳየው […]
“ለሲዳማ ቡና በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ ፣ ቀጣይ ጨዋታዎች ከቡድኑ ጋር በድል ለማሸነፍ እነጥራለን” “➖ ፋቢየን ፋርኖል
የሲዳማ ቡና ስፓርት በቅርቡ ካስፈረማቸው የውጭ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የቤኒን ብሔራዊ ተጨዋቾች የሆነው ግብ ጠባቂ ፋቢየን ፋርኖል ይጠቀሳል። በቀድሞ በፈረንሣይ ቦርዶ የተወለደው እና በቅርቡም የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፋቢያን የመሠለፍ ዕድልም አግኝቷል። ቤኒናዊው የ36አመቱ ግብ ጠባቂ ፋቢያን በዛሬው ምሽት ጨዋታ ለሁለተኛ ጊዜ ተሰልፎም ተጫውቷል ።ቡድኑም ማሸነፍ ችሏል ። አዲሱ የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ […]
” ዋንጫው ባይሳካም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውስጥ ብንገባ ደስ ይለኛል “- በረከት ወልዴ ( ወላይታ ድቻ )
ወላይታ ድቻ የ18ኛ ሳምንት ውጤቱን ድሬደዋ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ በድል አጠናቋል።በዛሬው ጨዋታ ለወላይታ ድቻ ከተቆጠሩት ጎሎች የመጨረሻዋን እና ወሳኟን ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ወጣቱ የአማካኝ ተጨዋች በረከት ወልዴ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። የዛሬውን ጨዋታ በተመለከተ “አረፍ ነበረ። ውጤቱ ስለሚያስፈልገን እና እነሱም ወደ ላይ ከፍ እንዳይሉ እና ለእኛም ውጤቱ አስፈላጊ ነበር። ስለዚህ 6 ነጥብ […]
“የእኔ ጊዜ ይመጣል በሚል ጠብቄ ነበር ፤ አሁን የኔ ጊዜ ነው ማለት እችላለሁ ” አቡበከር ኑሪ
የ18ኛው ሳምንት የዛሬው የምሽቱ የሃዋሳ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ በ1ለ1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው ላይ ከታዩ የሁለቱ ቡድኖች የመሸናነፍ እንቅስቃዎች በተጨማሪ በጅማ አባጅፋር በኩል ወጣቱ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በርካታ ዒላማቸውን ወደ ጎል የነበሩ ኳሶችን በግሩም ብቃት ተቆጣጥሮ ጎለ ከመሆን በማዳን የጨዋታው ትኩረት ያገኘ ተጨዋች ነበር ።ከጨዋታው በኃላ አቡበከር ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። […]