የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሁለተኛ ሆኖ ለማለፍ ዛሬ የመጨረሻውን እና ወሳኙን ፍልሚያ አቢጂያን ከኮትዲዮቫር አቻው ጋር በ10 :00 ሰዓት ያደርጋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አልያም አቻ መውጣት እና አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ለማለፍ በቂው ነው።በአንፃሩ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲዮቫር ከተሸነፈደግሞ በምድቡ በመጨረሻ ደረጃ የምትገኘው እና መውደቋን […]
ዜናዎች
“ከስምንት ዓመት በፊት የአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ፕሮጀክት ኦኜ ነበር በቴሌቪዥን ስመለከት የነበረው ዘንድሮ በተራዬ በዋልያዎቹ እገኛለሁ” ➖ሱሊማን ሀሚድ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዋናው የዋልያዎቹ ስብስብ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተካተተው እና ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻው 90 ደቂቃዎች ፍልሚያ አቢጂያን የሚገኘው ወጣቱ የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋች ሱሊማን ሀሚድ አንዱ ነው። የዋልያዎቹ የአሁኑ የኃላ መሥመር ደጀን ሱሊማን ሀሚድ ከዛሬ ስምንት አመት በፊት ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ የዋንጫን ከሶሰት አሰርት አመታት በኋላ ሲቀላቀል እሱ ያኔ የ15 አመት ታዳጊ እና […]
ዲ.ኤስ.ቲቪ ቀጣይ ስርጭቱን የሚካሄድባት ድሬ ደርሷል!
የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ አዘጋጅ ከተማ ድሬዳዋ ዝግጅቷን የጨረሰች ይመስላል። ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግን ጨዋታዎቹ በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈው የሱፐር ስፖርት ተንቀሳቃሽ መኪናዎች ከባህርዳር ከተማ ወደ ድሬ ገብተዋል። ተንቀሳቃሽ የቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮ እና የካሜራ ባለሙያዎች ቡድን የመጀመሪያው ልዑካኑ ድሬዳዋ ገብቷል። የፊታችን እሑድ መጋቢት 27 ጀምሮ በድሬዳዋ የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ በቀጣይ ቀናት ቀሪ የዲ ኤስ […]
ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ዛሬ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ! – ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል
ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና መርሀ ግብር ዛሬ መጋቢት 19/2013 ከቀኑ 10 : 00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብሩን ምክንያት አስመልክቶ ከቀናት በፊት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተጠቆመው ጀግናዋ አትሌት በስፖርቱ አለም ላበረከተችው በርካታ ተግባራት አስተዋፅ እና እውቅና በመስጠት መጪውን ትውልድ ማነቃቃት መሆኑን የኮሚቴው አባል የሆኑት አትሌት ገዛህኝ አበራ […]
የቀድሞ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ የጋናው አሳንቴ ኮቶኮ አዲስ አሰልጣኝ ሆነዋል !
ፖርቱጋላዊው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የጋና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ማሪያኖ ባራቶን የጋናው አሣንቴ ኮቶኮ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ሆነዋል።የጋናው ክለብ ከወራቶች በፊት ማክስዌል ኮናዱን ካሰናበተ በኃላ ፖርቱጋላዊውን ማሪያኖ ባራቶ በቦታው መተካቱ ሲሰማ አሰልጣኙም ወደ ጋና መድረሳቸው ታውቋል ፡፡ፖርቱጋላዊው ማርያኖ ባሬቶ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የዋና የአሰልጣኝነት ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት በረዳት አሰልጣኝነት ዳይናሞ ሞስኮ ፣ […]
የአይቮሪኮስት አና የኢትዮጵያን ጨዋታ ጋናዊው የመሀል ዳኛ ይኖሩታል !
በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከአይቮሪኮስት አቻቸው ጋር የመጨረሻውን የማጣሪያ ጨዋታው የፊታችን ማክሰኞ ያካሂዳል። ይህንን ጨዋታ ጋናዊው ኢንተርሽናል አርቢትር ዳንኤል አዬ ላሪያ ይመሩታል። የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂውን ጨዋታውም 60,000 ተመልካች የመያዝ አቅም ባለውና እግር ኳስ ፣ ራግቢ እና አትሌቲክስ በሚያስተናግደው በስታድ ዲ ኤቢምፔ ሁለገብ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታውን ክጋናዊው ኢንተርሽናል በዋና ዳኝነት ዳንኤል […]
” የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ምክንያት ሊቋረጥ ይችላል ” -፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ
በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል አሁን እየተካሄደ በሚገኘው የውድድር አመቱ የ16 ሳምንታት ጨዋታዎች ግምገማ እና ውይይት ላይ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፡ ከ13ቱ የሊጉ ባለ አክሲዮን ክለቦች የ10ሩ አመራሮች ፣ስራ አስኪያጅ፣ ቡድን መሪ ወይም አሰልጣኞች ተገኝተዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ የሊግ ኮሚቴው ውድድሩን የመራበት ሂደት አድናቆት የሚገባው ነው ሲሉ አድናቆታቸውን […]
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሾመ !
ከደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን በቂ ልምድ ያካበቱ ሲሆኑ፣ በርካታ ድሎችንም አሳክተዋል፡፡ እ.ኤ.አበ2015 እና 2016 የኬንያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ያነሱ ከመሆናቸው በተጨማሪ በ2015 የኬንያ ሱፐር ካፕ ምርጥ ስምንት አሸናፊም ሆነዋል፡፡ […]
ሲዳማ ቡና የ36 አመቱን ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል ! – ተጨዋቹ ለብሔራዊ ቡድኑ ግዴታ ወደ ቤኒን ተጉዟል
በፈረንሣይ ቦርዶ የተወለደው እና ከ10 ክለቦች በላይ የተጫወተው ቤኒናዊው ፋቢየን ፋርኖል ለሲዳማ ቡና ፊርማውን አካሄዶ ተጫዋቹ ለብሔራዊ ቡድኑ ግዴታ ወደ ቤኒን ተጉዟል።በእግር ኳስ ህይወቱ ለበርካታ ክለቦች የተጫወተው እና እ.ኤ.አ በ2020 ለቱርክ ኢርዝሩምስፖር ክለብ ለመጫወት ፈርሞ ምንም ጨዋታ ያላደረገው ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ በቀሪዎቹ የውድድር ጊዜያት ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማምቷል። በፈረንሳይ በተወለደበት ቦርዶ ከተማ ለሚገኘው እና በዋናው […]
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አዲሱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቅዳሜ ይገባል !
ከደቡብ አፍራካዊው ማሂየር ዴቪድስ የተለያየው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ሊቀጥር እንደሆነ ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ለኢትዮ ኪክ አድርሰዋል።ከጀርመናዊው ኤርነስት ሚድንዶርፕ ጋር ከተለያየ በኃላ ምክትሉን የ34 አመቱን ማሂየር ዴቪድስ በጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርገው ከሾሙ በኃላ ከአሰልጣኙ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ የአዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ቅድመ ሰምምንቶች መደረጋችውን ዛሬ ተሠምቷል።የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዛሬ ማለዳ ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው […]