የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያት በተለያዪ ከተሞች አየተዘዋወሩ እንዲደረጉ በሚል በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል። የሊግ ካምፓኒው ከሳምንታት በፊት የ16ቱን የውድድሩን ሳምንታት ጨዋታዎች ግምገማ አድርገው እንደነበር ይታወሳል።በወቅቱ የሊግ ኮሚቴው የቦርድ ፕሬዝዳንት የ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ ፉክክሩ በቀጣይ የሚካሄድባቸው ሀዋሳ እና ድሬዳዋ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ቀዳሚዎቹ አካባቢዎች መሆናቸውን ተናግረው ክለቦችን […]
ዜናዎች
DSTV የምሽት ጨዋታዎችን በቀጥታ ከድሬ እንዲያስተላልፍ ናሽናል ሲሚንት አፋጣኝ መፍትሔ ሰጥቷል !
የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አስተናጋጅ የድሬዳዋ ከተማ ከ17ኛ ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት የሚካሄደውን ውድድር ዛሬ ጀምራለች። በሞቃታማዋ ድሬ ዛሬ በተጀመረው እና በታሪካዊው የድሬጀዋ ስታዲየም በተካሄደው የ10:00 ሰዓቱ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ ያለ ጎል 0 ለ 0 ተለያይተዋል። ይህ ጨዋታ በDSTV የተላለፈ ቢሆንም በአንፃሩ ምሸት በ1:00 ሰዓት የተካሄደው የኢትዮጵያ ቡና እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ […]
“በርካታ ጎል የማስቆጠር አጋጣሚዎች አግኝተን ነበር”- ፍራንክ ናፓልን (ቅዱስ ጊዮርጊስ )
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከሰበታ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 51% የኳስ ቁጥጥር ነበረው እና 17 ጊዜ ወደ ጎል የሞከረ ሲሆን 6 ጊዜ ሂላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን አድርጓል ። አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዋና አሰልጣኝ እንግሊዛዊው ፍራንክ ናፓልን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ጀምረዋል። በዛሬው ጨዋታ ከሱፐር ስፖርት ጋር ያደረጉት ቆይታ። የመጀመሪያው አጋማሽ ያገኟቸው 9 የሚደረሱ ዕድሎች ያለመጠቀቻሁ […]
” የመክፈቻውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት ከነበረን ጉጉት የተነሳ ብዙ ኳሶችን አምክነናል ” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ( ሰበታ ከተማ)
የ17ኛው ሳምንት የመጀመሪያው ጨዋታውን ያደረገው እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር በባዶ ለባዶ ተለያየው የሰበታ ከተማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ባለመሸነፍ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ ሲሆን የሰበታ ከተማ ክለብ በዛሬውም ጨዋታ በርካታ የጎል ዕድሎችን አግኝተው ሆኖም ጨዋታው በአቻ ያል ጎል ተለያየትዋል ። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል። ብዙ የማግባት ዕድሎቹን […]
ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል!
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በትውልድ ኤርትራ ዜግነት ያለውን እና የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አንበል እንዲሁም የቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የነበረው ሮቤል ተክለሚካኤል አስፈርመዋል። ሮቤል ኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በ2019 የሴካፋው ውድድር ላይ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠ ሲሆን ሌላኛው የኢትዮጵያ ቡና ፈራሚ ተጫዋች ለደደቢት፣ እንዲሁም በከፍተኛ ሊግ ለከፋ ቡና ተጫዋች የነበረው ናትናኤል በርኸ ሲሆን ናትናኤል […]
“ከኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል የከተማው ተወካይ ክለብ ስትሆኑ አስተዳደሩ አቀባበልና ዕውቅና ይሰጣል”-ኮሚሽነር ዳዊት ትርፉ
በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር የሚሰለጥነው እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድቡ በአንደኝነት ለሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ ሽልማት ተበረከተለት ። ወልዲያ ከተማ በምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታውን እያካሄደ ያለውና በ38 ነጥብ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በመጀመሪያ ዙር አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቁና በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲገባ ለማበረታታትና ለመደገፍ ሲባል […]
” አገሬን ብሎም የተወለድኩባትን ከተማ ማገዝ በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ” ፉዓድ ኢብራም
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የድሬዳዋ ከነማ ተጫዋች የነበረው ፉዓድ ኢብራም የድሬዳዋ ስታዲየም የምሽት ውድድሮችን በጥራት እና የምሽት ጥላ ሳይኖር ጨዋታዎች እንዲታዮ የሚችሉ ኤል ዲ ፖውዛ ከድባይ በማስምጣት ለከተማው አስተዳደር ዛሬ አበርክቷል። በአሜሪካ ኑሮውን አድርጎ የነበረውና ለአሜሪካ ከ17 አመት እና 20 ዓመት በታች ቡድኖች በአለም አቀፍ ውድድሮች በመሣተፍ እንዲሁም በአውሮፖ በተለያዩ ሊጎች የተጫወተው የቀድሞ የኢትዮጵያ […]
የ50ኛው ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል ! – ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል !
የ50ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን በማስመልከት የዘንድሮው ሻምፒዮናው ለየት ባለ መልኩ ዛሬ ይጀመራል። ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስጠሩ በርካታ አትሎቶች የሚታዮበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዘንድሮው በተለየ ዝግጅት ደምቆ ዛሬ ይካሄዳል ተብሏል ። የዘንድሮው ሻምፒዮና የአገሪቱ አብዛኞቹ ክለቦች ፣ ክልሎች እና ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን በኮሮና ምክንያት ያለ ተመልካች የሚካሄድም እንደሆነም ተጠቁሟል ። ዘንድሮ ለ50ኛ […]
የቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በምሽት እንዲደረጉ ማሻሽያ ተደረገ !
የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያት በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል። አራተኛዋ የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስተናጋጅ ከተማ ድሬዳዋም ከነገ ጀምሮ ከ17ኛው ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት ያሉትን ውድድሮች የምታስተናግደ ይሆናል። በውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች በደማቅ አቀባበል ድሬደዋ ገብተዋል ። ታሪካዊው የድሬዳዋ ስታዲየም ለመጀመሪያ ጊዜ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን በምሽት እንደሚደረጉ ተረጋግጧል ።ከዚህ በፊት […]
ሉሲዎቹ ልምምዳቸውን ዛሬ በይፋ ጀምረዋል ! የሴቶች ሊግ ኮከብ ተጨዋች አለመካተት አነጋጋሪነቱን ቀጥሏል !
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው ከቀናት በፊት ጥሪ ያቀረቡላቸውን 26 ተጨዋቾችን ይዘው ዋልያዎቹ ዝግጅት ሲያደርጉበት በነበረው የካፍ የልህቀት ማዕከል ዛሬ ረፋድ ሉሲዎቹም ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።ኢትዮጵያ በሴቶች ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ላለበት የሴካፋና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የተጨዋቾች ምርጫ አጠናቀው ዛሬ የመጀመርያ ልምምዳቸውንም አከናውነዋል።አሰልጣኝ ብርሃኑ የቀድሞ ረዳት አሰልጣኝ የነበረችውን መሠረት ማኔኝ አሰናብተው […]