በአሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚሰለጥነው ሰበታ ከተማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ከወራጅ ስጋት ተላቆ ነጥቡን በተሻለ ሆኖ ለማጠናቀቅ ዛሬን ጨምሮ ሶስት ጨዋታዎች ይቀሩታል። የቡድኑ የዘንድሮው ስብሰብ አንፃር ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የተጠበቀው ባይሆንም በሊጉ በመቆየቱ በቀጣይ የቡድኑን ችግሮች የሚፈትበት ጊዜ ይኖረዋል። በአንፃሩ ክለቡ ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ከተጨዋቾች ጋር ችግሮቹን የሚፈታ ካልሆነ […]
ዜናዎች
“የዛሬው ሶስት ነጥብ ከኛ በላይ ለድሬዳዋ ደጋፊዎች እና ለድሬ የስፓርት አፍቃሪዎች ይገባቸዋል “–ኢታሙና ኬሙይኔ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል። የድሬዳዋን ማሸነፊያ ግቦች ሪችሞንድ አዶንጎ ፣ኢታሙና ኬሙይኔ እና ሰዒድ ሀሰን በራሱ ላይ ሲያስቆጥሩ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ሙጂብ ቃሲም አስቆጥሯል። ከጨዋታው በኃላ ኢታሙና ኬሙይኔ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። በቅድሚያ ጎል በማስቆጠሩ እና በጨዋታው በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለህ ” አመሠግናለሁ ።በቅድምያ ለእግዚአብሔር ምስግና […]
” ሀገሬን በየትኛውም የውድድር መድረክ መወከል በመቻሌ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል “- ሽመልስ በቀለ
በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ አመታት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው እና በተለየ መልኩ በዘንድሮው የግብፅ ሊግ በግሉ የተሳካ ጊዜን በማሳለፍ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ሽመልስ በቀለ ቡድኑ አሸንፎ የወጣበት ወሳኝ ጎል አስቆጥሯል። በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በትላንትናው የ21ኛ ሳምንት ጨዋታ የሽመልስ ምስር ኤል ማካሳ የቀድሞ የጋቶች ፓኖም ክለብ የሆነውን አል ጎናን በሜዳው አስተናግዶ በ90ኛው ደቂቃ […]
“ዕድላችን ይሄ ነበረ ብዬ የማስበው ለዛ ነው በጣም ያዘንኩት “-ጀማል ጣሰው ( ወልቂጤ ከተማን)
በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሊጉ የተቀላቀለውና በዘንድሮው የቤትኪንግ ጅማሮ ላይ ጠንካራ ቡድን የነበረው ወልቂጤ ከተማ በዛሬው ጨዋታ ከሐዋሳ ከተማ ጋር ያለ ጎል መለያየቱ ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ላይ በጭንቀት እንዲጠብቅ ያደረገዋል። የዛሬው ጨዋታ እንደተጠናቀቀ በወልቂጤ ከተማ በኩል ተጨዋቾቹ እያዘኑ ከሜዳ ሲወጡ ታይተዋል።በተለይም የወልቂጤ ከተማው ግብ ጠባቂ እና የቡድኑ አምበል ጀማል ጣሰው የዛሬው ጨዋታ ሲጠናቀቅ ከሜዳው […]
” የቡና ደጋፊ በስታዲየሙ ቢኖር በራሱ አንድ ደስታ ነበር: የእኔ ሪከርድ ተሳክቷል፤ የክለቤ ውጤት ፣ አልተሳካም በጣም አዝኛለሁ “- አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና )
ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አቡበከር ናስር በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል በማስቆጠር ሪከርድን ሰብሯል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ላይ 9ኛ ፣ 36ኛው ፣90 ደቂቃ ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ የውድድር ዘመን ጎሎቹን ቁጥር 2ት አድርሷል፡፡ አቡበከር ናሰር በዛሬው ጨዋታ አራተኛ ጊዜ ሃትሪክ ከመያዙ በተጨማሪም በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ላይ ሁለተኛውን ሀትሪክ በመያዝ ሌላ ተጨማሪ ሪከርድ ይዞም ወጥቷል። […]
ዋልያዎቹ 16 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው !
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የኤፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶች እግርኳስ ቡድን ወደ ካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ6 ሚሊዮን ብር እና የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከ8 ሚሊዮን ብር ሽልማት እና 3 ሚሊዮን ብር ለፕሮግራሙ ወጪ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን 10 ሚሊዮን ብር አበርክቷል ። […]
የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ ቅሬታውን አቀረበ !
በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አልጀርስ ላይ የትላንት ምሽቱ የሞሮኮው ዊይዳድ ካዛብላንካ ከአልጄሪያው ሚሲ አልጀርስ ጋር በ1 ለ1 አቻ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩትን ኢትዮዽያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቻቸው ላይ የሞሮኮው ዊይዳድ ካዛብላንካ የዳኝነት ቅሬታውን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ልኳል ፡፡ . የዊይዳድ ክለብ በትዊተር ገፁ እና ለመገናኛ ብዙሃን […]
ዐፄዎቹ ዋንጫውን በቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ይረከባሉ – ዋንጫው ግን አሁንም አልደረሰም !
የ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ለሆነው የፋሲል ከነማ ቡድን የዋንጫ ሽልማት ስነስርዓት በቀጣዮ ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 14/ 2013 ፋሲል ከነማ ከሐዋሳ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ የሻምፒዮናውን ዋንጫ እንደሚያንሳ ታውቋል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የዋንጫው ስነስርዓት የፊታችን ቅዳሜ ለማካሄድ የተወሰነ ሲሆን የዋንጫ አሰጣጥ ስነስርዓት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መዘጋጀቱም ታውቋል። በአንፃሩ ዘንድሮ የተለየ የተሰኘው […]
“ባህርዳር ከተማ በጣም ጥሩ ስብስብ ነው ፤ እንደ ቡድን ብንጫወት ዋንጫውን እናገኝ ነበር፤ ደጋፊው ከዋንጫ በላይ የሚገባውም ነበረ “-ምንይሉ ወንድሙ
ምንይሉ ወንድሙ ለባህርዳር ከተማ ወሳኝ ከሚባሉት ተጨዋቾች አንዱ ነው። ባህርዳር ከተማ ትላንት ለሁለተኝነት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 አች ሲለያዩ ምንይሉ ጎል አስቆጥሮ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸውን ጎሎች 6 አድርሷል። ኢትዮኪክ ከምንይሉ ወንድሙ ጋር ቆይታ አድርገናል። ኢትዮ ኪክ :- የዘንድሮ በሊጉ ያለህ አቋም እንዴት ይገለጻል ? ምንይሉ :- ዘንድሮ ወደነበርኩበት የበፊት አቋሜ ለመመለስ እየጣርኩ […]
” በርግጠኝነት ሐዋሳ ላይ እንደማገባ አውቅ ነበር ፤ ለአሰልጣኙም ካላገባው ቦርሳዬን ይዤ እንደምሄድ ነበር የነገርኩት ” -አብዲሳ ጀማል
የአዳማ ከተማው አብዲሳ ጀማል በውድድር ዓመቱ ዘጠኝ ጎሎች አስቆጥሯል። ምንም እንኳ አዳማ ከተማ በቀጣይ አመት ከሊጉ መሰናበቱን ያረጋገጠ ቢሆንም የተጨዋቹ የግል ብቃት አድናቆት የተቸረው ነው። የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ አብዲሳ በውድድር ዓመቱ ካስቆጠራቸው ዘጠኝ ጎሎች አምስቱ በሐዋሳ ከተማ ላይ የተቆጠሩ ናቹው። ይህን እና ተጨማሪ ጥያቄዎችን በተመለከተ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፓርት ጋር አብዲሳ ጀማል ቆይታ አድርጓል። ካስቆጠራቸው […]