ዜናዎች

የፈረሰኞቹ አዲሱ አሰልጣኝ ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች የታንዛኒያው ሲምባ ለማሰልጠን ሲቪያቸውን መላካቸው ተሰማ !

አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ   ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች ፈረሰኞቹን ከተረከቡ ከሁለት ወር ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላ ወላጄ አባቴ አርፏል በማለት ከቀናቶች በፊት ወደ ሀገራቸው መጓዛቸው ይታወቃል። ይሁንና የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ሰርቢያዊ  ዝላትኮ ክራምፖቲች ሀዘን ብለው በተጓዙ በቀናት ልዩነት ከታንዛኒያው ሲምባ ጋር ከትላንት በሰቲያ ጀምሮ ስማቸው እየተነሳ ይገኛል። የታንዛኒያው ፉትቦል ቲሺ ትላንት ባሰፈረው መረጃ የታንዛኒያው ሲምባ ክለብ […]

ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ !

በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዚምቧቤ እና ከጋና ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ ምንም እንኳ ከምድቧ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ባትችልም፤ ቀሪ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎቿን ህዳር 2 ከጋና ጋር ጆሀንስ በርግ እንዲሁም ህዳር 5/2014ዓ.ም ከዚምቧቤ ጋር ሀራሬ ላይ የምትጫወት ይሆናል። እነዚህን ጨዋታዎች ለማድረግ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን እነዚህ […]

ዜናዎች

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጅቡቲን 7 ለ 0 አሸነፈ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 20 – እስከ ጥቅምት 30/2014 ለሚካሄደው የምሥራቅና የሴካፋ ውድድር ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታውን በድል ጀምሯል። በዮጋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ የታዳጊዎች ውድድር ኢትዮጵያ ጅቡቲን 7 ለ 0 አሸንፋለች። ጎሎቹን ረድኤት አስረሳኸኝ ሶስት ጎሎች አስቆጥራ ሐትሪክ ስትሰራ ፣ ቱሪስት ለማ ሁለት ጎሎች እፀገነት ግርማ እና ቤተልሔም በቀለ አንድ […]

ዜናዎች

ጋና ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ መደረጉን በመቃወም የስታዲየም ለውጥ ጠየቀች !

የጋና እግር ኳስ ማህበር በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በባህርዳር ስታዲየም ዕገዳ ምክንያት  ወደ ደቡብ አፍሪካ መደረጉን በመቃወም በይፋ የተቋሞ ድምፁን አሰምቷል ።  የጋና እግር ኳስ ማህበር ባለፈው ዓርብ  ለካፍ  እና ለፊፋ በላከው ደብዳቤ በ2022 የአለም ዋንጫ ማጣርያ  ከደቡብ አፍሪካ በ1 ነጥብ ልዩነት  በሁለተኝነት ደረጃ በሚገኝበት አገር ላይ መደረጉ ስህተት ነው በማለት የጨዋታውን […]

ዜናዎች

ሰበታ ከተማ በፊፋ ዕገደ ሊጣልበት መሆኑ ተሰማ!

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በሁለተኛው ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ በ11ኛ ደረጃ የሚገኘው የሰበታ ከተማ ቡድን ከውጭ አገር አስፈርሞት ነገር ግን ደሞዝ  ባልከፈለው  ተጨዋች ጋር በተያያዘ በፊፋ ጠንከር ያለ እገዳ ሊተላፍበት መሆኑ ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። እንደ መረጃው ከሆነ ሰበታ ከተማ በክለቡ ውስጥ አስፈርሞት የነበረና አሁን ላይ ከቡድኑ ጋር እንደሌለ በተነገረለት የውጭ ተጨዋች ከ5ሺ ዶላር በማይበልጥ ያልተከፈለ […]

ዜናዎች

የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደት ዛሬ ተጎብኝቷል!

62 ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም አለው የተባለለት እና ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የ2ኛው ምዕራፍ ግንባታ ጅማሮ በ900 ቀናት ውስጥ ከ5 ነጥብ 57 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ አስመልክቶ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ ፣ የኢትዮጵያ እግር […]

አፍሪካ ዜናዎች

ሉሲዎቹን ካሸነፉት የዮጋንዳ ተጨዋች – አንድ ተጨዋች በደስታ ራሷን ሳተች !

በሞሮኮ አስተናጋጅነት በ2022 ለሚከናወነው የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ ለማለፍ በመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በዮጋንዳ 2 ለ 0 ተሸንፈው የነበሩት ሉሲዎቹ ዛሬ በ10:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የመልስ ጨዋታ ለማሸነፍ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ  በመለያ ምቶች   ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል ።   የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቀዳሚ ሆኖ በ21ኛው ደቂቃ በሴናፍ ዋቁማ ጎል ማስቆጠር ሲችሉ፣ ከእረፍት በፊት ካገኟቸው […]

ዜናዎች

የግብፅ ሊግ ዛሬ ተጀምሯል- ሽመልስ በአዲሱ ክለቡ ነገ ጨዋታውን ያደርጋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ሸመልስ በቀለ  የግብፅን ክለብ ኤል ጎውናን ከተቀላቀለ በኋላ ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ለአዲሱ የውድድር ዓመቱ የዝግጅት እና የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። የአዲሱ የውድድር ዓመት የግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ መጀመሩን ተከትሎ ሶስት ጨዋታች ተደርገዋል። በመርሐ ግብሩም መሠረት የሽመልስ በቀለ ኤል ጎውናን ነገ ( ማክሰኞ )አመሻሽ ላይ በሜዳው ጨዋታውን ያደርጋል ።  

ዜናዎች

ካፍ ያስተላለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ ተገለፀ !

  የባህርዳር ስታድየም በካፍ ልዑክ ተገምግሞ በቀጣይ ኢንተርናሽናል ጨዋታወችን እንዳያስተናግድ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተላለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያላገናዘበና እየተሰሩ ያሉ ስራወችን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ። በመግለጫው ካፍ ለእገዳው በምክንያትነት ካነሳቸው አስተያየቶች መካከል የተጨዋቾች መልበሻ ክፍል ግብዓቶችን ማሟላት፣የVIP ጣራ ስራ፣ የሚድያ ክፍል ማዘጋጀት፣ የተጠባባቂ ተጨዋቾች መቀመጫ፣እንዲሁም የሜዳ […]

ዜናዎች

ሉሲዎቹ የነገውን ከዮጋንዳ አቻቸው ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ነገ ላለበት የመልስ ጨዋታ እና ከቀናት በፊት ስለ አደረጉት እንዲሁም የቡድኑን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እና አምበሏ ሎዛ አበራ ወሎ ሰፈር በሚገኝው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በመግለጫው እንደተናገሩት ከዮጋንዳ በነበረው ጨዋታ በድኑ 2 […]