ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ዳኛን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው በቀረበ ሪፖርት /ሃምሳ ሺህ/ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 24ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 12 ጎሎች በ10 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 10 በጨዋታ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ነው። በሳምንቱ 26 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች ቀይ ካርድ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሐሙስ ግንቦት 10 […]

አፍሪካ ዜናዎች

” በአካዳሚያችን የሚጫወቱ ታዳጊ ተጨዋቾቻንን ወደ አውሮፓ አገራት ለማጫወት ለእኛ ይሄ ከባድ አይደለም፤ በቅርቡ የምንተገብረው ነው”የ3 Points አካዳሚ ዳይሬክተር  አቶ ሳሙኤል ተገኝተው

    የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊዎች እግር ኳስ ስልጠና ከሚሰራው የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ (3 Points) ፕሮጀክት ጋር በጋራ ለመስራት በጥር ወር 2014 በይፋ የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸው ይታወሳል። እናም ከወራቶች በፊት የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ ተቋም ይፋዊና ከስምምነቱ በኋላ ቀጥታ ወደ ሥራ ገብቶ ታዳጊዎችን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን – ካፍ የልህቀት ማዕከል በማሰልጠን ከፍተኛ የሆነ ስራን […]

ዜናዎች

#የዋልያዎቹ ቀጣይ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ !

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ በጊዜያዊነት እንዲመሩ የኢ/እ/ፌ ቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና እና ረዳት አሰልጣኝነት መሾሙ የሚታወስ ሲሆን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሠረት በቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙትን እና ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድኑ ልምድ ያላቸውን አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን ሾሟል።

ዜናዎች

# አሰልጣኝ አስራት ኃይሌን የከተማው አመራሮች በቤቱ ተገኝተው ጠይቀዋል! -የ250ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እግር ኳስን በታማኝነት ላገለገለው አንጋፋው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው) ለሕክምና ወጪ የሚውል የ250ሺ ብር ድጋፍ አድርገው በመኖርያ ቤቱ ጠይቀውታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት በሴካፋ ያመጣው ድል በእግር ኳስ ፌድሬሽን በሰጠው አመራርነት በርካታ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሊቪዥን ስርጭት ሽፋን አያገኙም!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር በሃዋሳ ከተማ ከ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ውድድሩ በቀጥታ የሱፐር ስፖርት ሽፋን እያገኘ እስከ 24ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስለሆነም አክሲዬን ማህበሩ ከመልቲቾይዝ አፍሪካ(ዲኤስቲቪ) ጋር ባለው የብሮድካስት ውሉ መሰረት በአመቱ የሚተላለፉ ጨዋታዎች ጋር በተያያዘ በሃዋሳ ከተማ የሚደረጉ ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 23ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 23ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 17 ጎሎች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 15 በጨዋታ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ነው። በሳምንቱ 46 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አምስት ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ግንቦት 05 […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#የተጨዋቾች የደሞዝ ክፍያ ጉዳይ አሁንም ምላሽ ማግኘት አልቻለም!

# ኑሮን ለማሸነፍ የንግድና ራይድ ሹፍርና የጀመሩ ተጨዋቾች መኖራቸው ተሰምቷል! የኢትዮዽያ ክለቦች የተጨዋቾቾን ደሞዝ ያለመክፈል ጉዳይ ከዓመት ዓመት በስፋት ቀጥሎ ዘንድሮም በይፋ በቀጥታ የ DSTV ስርጭት የዋልያዎቹ የቀድሞ ተጨዋች እና የወልቂጤ ከተማ አምበል ጌታነህ ከበደ እስከመናገር ደርሷል። በርግጥ በሊጉ ከሚገኙት 16 ክለቦች መካከል የወልቂጤ ከተማ እና የለገጣፎ ተጨዋቾች አሳዛኝ ችግር በይፋ ቢናገሩም አሁን በዋናው ሊግ […]

English ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት ተለያይተዋል! Ethiopia national team parts ways with head coach Wubetu Abate

ከመስከረም 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ውበቱ አባተ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የአሰልጣኙን መልቀቂያ በመቀበሉ በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለነበራቸው ቆይታ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው መልካም የሥራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ልባዊ […]

አፍሪካ ዜናዎች

#ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ተጠባቂውን ጨዋታ ይመራሉ !

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)በቀጣይ ሳምንት በግብፅ ሊግ በመሪነት ደረጃ ላይ የሚገኘው  አል አህሊ  ከሱዳኑ አል-ሂላል ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ   ኢትዮጵያዊውን  አርቢተርች እንዲመሩት መርጧል ።   በካይሮ ኢንተርናሽናል ሴንት አል አህሊን ስታደየም  የሚጀረገውን የህን የአል-ሂላል እና አል-አህሊ የካፍ ሻምፒዮስ ሊግ  ስድስተኛው እና የመጨረሻው ዙር  ጨዋታን  ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።   ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ […]

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ በስዊዘርላንድ ሊግ  ቡድኑን ለድል አብቅቷል

በስዊዘርላንድ ታዳጊ  ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ስፍራ  ተጨዋች ያሳለፈው የ21  አመቱ   ትውልደ ኢትዮጵያዊ  ቅዱስ ሃይለስላሴ  ቡድኑ አሸንፎ እንዲወጣ ያሳቻሉትን ሁለት ወሳኝ ጎሎች አስቆጥሯል። የአማካይ ስፍራው የወደፊት ኢንጂነር የሚል ስያሜን ያተረፈው   ኢትዮጵያዊያዊው ታዳጊ  ቅዱስ  ኃይለ ሥላሴ በስዊዘርላንድ ዙሪክ ኤፍ ሲ  ሁለተኛው ቡድን የሚጫወት ሲሆን ከሦስት ወራት በኃላ ከጉዳት መልስ በፈረንጆቹ  የውድድር ዓመት  የመጀመርያውን ጨዋታውን አድርጓል። በስዊስ ከዋው […]