Athlete Derartu Tulu
አትሌቲክስ

ለክብርት ጀግና ለኮ/ር ደራርቱ ቱሉ ዕውቅ እና ሽልማት ተበርክቷል !

በዛሬው የስካይ ላይት ሆቴል ለኮ/ር ደራርቱ ቱሉ በተደረገላት የእውቅና፣ ሽልማት እንዲሁም የአክብሮቶች ልዩ ፕሮግራም ላይ የሚከተሉት ሽልማቶች ተበርክቷል! ፌደራል ማረሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1ኛ ደረጃ የተሰጠ የክብር ኒሻን ሽልማት ተበርክቶላታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአያት የሚገኘውን ትልቁን አደባባይ በስሟ ተሰይሟል የሁለት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ከከተማ አስተዳደሩ ተበርክቶላታል ኦሮሚያ ክልል አምስት ሚሊየን እና ሱሉልታ የስፓርት አካዳሚ […]

Derartu Tulu
አትሌቲክስ ዜናዎች

ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ዛሬ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ! – ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና መርሀ ግብር ዛሬ መጋቢት 19/2013 ከቀኑ 10 : 00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብሩን ምክንያት አስመልክቶ ከቀናት በፊት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተጠቆመው ጀግናዋ አትሌት በስፖርቱ አለም ላበረከተችው በርካታ ተግባራት አስተዋፅ እና እውቅና በመስጠት መጪውን ትውልድ ማነቃቃት መሆኑን የኮሚቴው አባል የሆኑት አትሌት ገዛህኝ አበራ […]

አትሌቲክስ

ኢትዮጵያን በቶኪዮ ፓራሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተረጋገጡ!

አምስት አባላት ያካተተው የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን በቱንዚያ አገር አስተናጋጅነት እ ኤ አ ከማርች 14-21/2021 እየተካሄደ በሚገኘው የ2021 የቶክዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ የሚኒማ ማሟያ ( ማጣሪያ ) የውድድር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ። ከብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አንዱ የሆነው አትሌት ታምሩ ከፍያለው በ1500 ሜትር 03:56 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ጨርሶ በመግባት ለቶኪዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያን የሚወክል መሆኑ ታውቃል ። […]

አትሌቲክስ

የቶኪዮ ኦሎፒክ ዝግጅት እክል ገጥሞታል!

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውጥረት ተካርሮ መቀጠሉን መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ዛሬ በኔክሰስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ያረጋገጠም ሆኗል።በተለየም ፍጥጫው በፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እና በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኦሎምፒክ ኮሜቴ ፕሬዝዳንት መካከል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንደሚታወሰው የኦሎምፒክ ውድድሮች በመጡ ቁጥር ተመሳሳይ ውጥረቶች ከዚህ […]

አትሌቲክስ

የአትሌት ለምለም ኃይሉ ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ፀደቀ !

በፈረንሳይ ሌቪን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የቤትውሰጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አትሌት ለምለም ያስመዘገበችው የ 4 01.57 ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ ከ 20 ዓመት በታች የቤት ውስጥ የ 1500 ሜትር የዓለም ሪኮርድ ሆኖ ማፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ በድህረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ ክብረወሰን ሰበረች!

ኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በፈረንሳይ ሊቫን በተረደረገው የአለም የቤት ውስጥ በ1500 ሜትር ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እ.ኤ.አ. በ 2014 (በ3 55.17) ተይዞ የነበረውን አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ3 53.09 ሰዓት በመግባት አዲስ የዓለም የቤት ውስጥ ሪኮርድ ባለቤት ሆናለች

አትሌቲክስ ዜናዎች

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፈረንሳይ ሌቪን ደምቀው አመሹ

በፈረንሳይ ሌቪን በተደረገው የ2021 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።በሴቶች የ1500ሜትር የአምናው የሌቫን አሸናፊ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዘንድሮ በርቀቱ 3: 53.09 ሪከርዱን ጭምር በመስበር አሸናፊ ሆናለች። ከቀናት በፊት የአለም አትሌቲክ ፌዴሬሽን ባሳወቀው መሠረት ያለፈው ከ20 አመት በታች በሌቫን ያሸነፈቸው የ1500ሜትር ውድድር አዲስ የአለም ሪከርድ ሆኖ እንዲመዘገብ የተደረገላት አትሌት ለምለም ሃይሉ በምሽቱ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በቀናት ልዪነት ሌላኛውን ድል ደግማለች !

ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ላቪስ በተደረገው የ1500 ሜትር የቤትውስጥ ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት በገንዘቤ ዲባባ ለ7አመት ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ የሰበረችው ጀግናዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዛሬ ደግሞ በ 800 ሜትር በቁጥሬ ዱለቻ እ.ኤ.አ 1999 ተይዞ የነበረውን የ800ሜትር 1 :59.17 በማሻሻል 1: 57.52 አዲስ የአለም ፈጣኑን ሰአት አስመዝግባለች።