በጀርመን -ካርልስሩሄ በተካሄደው የአለም የቤት ውስጥ የ3000ሜትር የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮዽያዊው አብዲሳ ፈይዛ የተባላው የ17አመት ታዳጊ የመጀመርያውን የቤት ውስጥ ውድድር በ7፡40.35 በቀዳሚነት አሸንፏል። መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን :- https://www.instagram.com/ethio_kick ድረ ገጻችንን :- https://ethio-kickoff.com
አትሌቲክስ
በፌዴሬሽን ፕሬዝደንትና በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተመራው ልዑካን ቡድን መቐለ ደርሰዋል!
From Abdu Muhammed በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል የፌዴሬሽኑ ም/ል ፕሬዝደንት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋዩ አቶ ተፈራ ሞላ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ ሳራ ሃሰን ፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ ፣ አትሌት መሠለች መልካሙና ዶ/ር ተስፋዬ አስገዶም እንዲሁም የጽ/ቤት ተወካዩ አቶ […]
” ለንደን የመጣሁት ለማሸነፍ ነው “አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እሁድ ከሚደረገው የለንደን ማራቶን አስቀድሞ በሰጠው አስተያየት አሁንም የረጅም ርቀት ታላቁ አትሌት መሆኑን ገልጿል። የ 40ዓመቱ ታሪክ አይሽሬው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሶስት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ፣ 17 የሀገር አቋራጭ ክብሮች እንዲሁም የ 5,000 እና 10,000ሜትር ሪከርድን ለአስራ አምሰት እና አስራ ስድስት ዓመታት የግሉ አድርጎ አቆይቷል። ” ራሴን ከኪፕ ቾጌ ጋር ማፎካከር […]
ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ የቫሌንሺያን ግማሽ ማራቶን አዲስ ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች!
From Abdu Muhammed በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በ62:50 በሆነ ሰዓት አዲስ የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸንፋለች። የ23 ዓመቷ ድንቅ እና ውጤታማ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሮጥ አዲስ ታሪክ ሰርታለች። የዓለማችን የ5000 ሜትር እና የ10,000 ሜትር በለሪከርድ ለተሰንበት ግደይ የቫሌኒሽያውን ግማሽ ማራቶን በ 01 : 02 […]
ጀግኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶን ላይ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅቷል!!
ተጠባቂው የበርሊን ማራቶን መስከረም 16/ 2014 ይካሄዳል። የ39 አመቱ ቀነኒሳ በቀለን እእአ ከ2019 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ሀጂ አዴሎ የቀነኒሳን ብቃት ከባለፈው የበርሊን ማራቶን ጋር አነጻጽረው አሁን በጣም በተሻለ ብቃት ላይ እንደሆነና ክብረ ወሰን ለማሻሻልም የሚያስችል አቋም ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ቀነኒሳ እእአ በ2019 በተካፈለበት ማራቶን በኬኒያዊው ኢሉድ ኪፕቾጊ የተያዘዉን ክብረወሰን ለጥቂት (ለሁለት ሰከንድ) ሳይሰብረው መቅረቱ […]
– በቶኪዮ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድኑ በመዝጊያው ስነስርዓት በባህል ልብስ በዛ ብሎ ታይተዋል ! – መቼ ይገባሉ ? አቀባበል ? እነማን ነበሩ? ከ250 ሚሊየን ብር በጀት ሆኗል ?
የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በደማቅ የመዝጊያ ስነ-ስርአት ተጠናቋል። በ2020 የቶክዮ የመዝጊያ ስነ-ስርአት ሲጠናቀቅም በመክፈቻው ላይ ያልታየው በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የልዑካን ቡድን በባህል ልብስ በስታዲየም ውስጥ በዛ ብሎ ታይል። ኢትዮዽያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ4 ስፖርቶች ያገኘችው 4 ሜዳሊያዎች ብቻ ነበር (1 ወርቅ ፤ 1 ብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች) ከአፍሪካ 3ኛ ከዓለም 56ኛ ደረጃ አጠናቃለች። […]
አትሌት ሀብታም በ800 ሜትር የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆናለች !
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 800 ሜትር ለፍፃሜው የበቃችው አትሌት ሀብታም አለሙ ፍፃሜውን በ 1:57.56 በስድስተኛ ደረጃ ጨርሳለች ። አትሌት ሀብታም የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብም ችላለች። ርቀቱን በትውልድ ሱዳናዊት በዜግነት አሜሪካዊት የሆነችው የ19 ዓመቷ አቲንግ ሙ 1:55 .21 በሆነ ምርጥ ሰዓት አሻሽላ በቀዳሚነት አሸንፋለች። ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር ያሳየችው ጥረት በርቺ ልትባል ይገባል። አትሌት ሀብታም […]
– በ5ሺህ ወንዶች በቶኪዮ የሚገኘው ሙክታር በሰዎች ስሜታዊነት በዛሬው ውድድር አይሰለፍም ?
የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮዽያዊያን የሚሳተፉበት ውድድር ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 27/2013 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ይደረጋል።በዚህ ርቀት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከ1ኛ – 4ኛ ወጥተው ባመጡት ፈጣን ሰአት እንደሆነ ይታወቃል። በአንፃሩ በ5ሺህ ሜትር በተደጋጋሚ በአጨራረስ የሚታወቀውና በርቀቱ ስመጥር የሆነውን የዓለም ድንቅ አትሌት ሞህ ፋራን ጭምር ያሸነፈው ሙክታር እንድሪስ በሀገር ውስጥ […]
– አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5 ሺ ሜትር ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል !
ትላንት ምሽቱን ወደ ቶኪዮ ያመራው 4ኛዙር የኢትዮዽያ ልዑካን ቡድን ቶኪዮ በሰላም መድረሱ ታውቋል። በአራተኛ ዙር ትላንት የተጓዘው የወንዶች 5000 እና 1,500 ሜትር የያዘው የኦሎምፒክ ቡድን መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ለዑካን ወስጥ የነበረው እና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝርዝር ያልተካተተው ሙክታር እድሪስ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ጥረት ወደ 5 ሺ እንዲገባ ተደርጓል ። በዚህ መሠረት ውጤታማው ድንቅ አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5ሺህ […]
“ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ የታላላቆቼን ምሩፅ ይፍጠር፣ሀይሌ ገብረ ስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለን ታሪክ በመድገሜ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ ” – አትሌት ሰለሞን ባረጋ
በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት ከ13 ዓመት በኃላ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያሰገኘ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል። ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አፈትልኮ በመውጣት ርቀቱን በ27:ከ43.22 በሆነ ጊዜ በአስገራሚ መልኩ ማሸነፍ ችሏል። በውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ዮጋንዳውያኑ አትሌቶች […]