Letesenbet Gidey #Fair Play Award አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሽልማቱን ያገኘችው በቡዳፔስቱ የአለም ሻምፒዮና በ10ሺህ ሜትር ውድድር በመጨረሻው ቅፅበት አትሌት ሲፋን ሃሰን ስትወድቅ ለመርዳት መሞከሯን ተከትሎ Fair Play Award መልካም ተግባር ተሸላሚ ሆናለች። ’s world 10,000m silver medallist Letesenbet Gidey has been named winner of the International Fair Play Award #AthleticsAwards
አትሌቲክስ
.ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በቫሌንሽያ ማራቶን ታላቅ ድልን ተቀዳጅተዋል!
በወንዶች አትሌት ሲሳይ የቦታውን ክብረወሰን ሰብሯል! ከወሊድ መልስ አትሌት ወርቅነሽ ዳግም ወርቁን አጥልቃለች ! በ2023 የአለም የማራቶን ውድድር አንዱ የሆነው የቫሌንሺያ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቋል። ኢትዮጵያዊው ሲሳይ ለማ በወንዶች ገና ከጅምሩ ጠንከር ያለ ፍጥነት በመሮጥ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዳዊት ወልዴ እና ኬኒያዊው ኪቢወት ካንዲ ጋር መሪነቱን ቢቀላቀልም ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በመምጣት ውድድሩን በ 2፡01 48.በሆነ […]
በሻንጋይ ማራቶን አትሌት ስራነሽ ይርጋ ዳኜ አሸናፈች!
በሻንጋይ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ስራነሽ ይርጋ ዳኜ ማሸነፍ ችላለች።አትሌቷ 2:21:28 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ማጠናቀቅ የቻለችው። በወንዶች የሻንጋይ ማራቶን ኬኒያዊው አትሌት ፊሊሞን ኪፕቱ ኪፕቹምባ 2:05:35 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡
@The Great Ethiopia Run#ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደቀድሞ ባይሆንም በርካታቶች ተሳትፈውበት ተጠናቋል #
የ23ኛው ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ ተካሄዷል። በውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ በውድድሩ ዲፕሎማቶች፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የክብር እንግዶች እና እንደቀድሞ ባይሆንም በርካታ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል። በዚህም በወንዶች ዘርፍ አትሌት ቢኒያም መሃሪ ሲያሸንፍ÷በሴቶች ደግሞ መልክናት ውዱ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡ ውድድሩ ላይ የሚያሳዩ ፎቶዎች ሼር ያድርጉን […]
ኢትዮጵያዊውያን አትሌቶች የኒውዮርክ ማራቶንን አሸነፈዋል !
Hellen Obiri and Letensebet Gidey ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ በአሜሪካ ኒውዮርክ ማራቶን 2:04:56 የቦታውን ሪከርድ በመስበር ሲያሸንፍ በሴቶች ኬኒያዊቷ ኦብሪ አንደኛ ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ሆናለች። @2023 New York marathon. Men’s 1.Tamirat Tola 2:04:58 2.Albert Korir 2:06:57 3.Shura Kitata 2:07:11 Women’s Results 1.Hellen Obiri 2:27:23 2.Letensebet Gidey 2:27:29 3.Sharon Lokedi 2:27:33
የጃፓን መንግስት ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት አበረከተ!
የጃፓን መንግስት ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠውን የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አበርክቷል፡፡ አትሌት ደራርቱ በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለው የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ላደረገችው አስተዋጽኦ ነው ሽልማት የተበረከተላት፡፡ አትሌት ደራርቱ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሺንዞ አቤ በፈረንጆቹ 2014 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር እንዲወያዩ እድርጋ እንደነበር ተመላክቷል፡፡ በአውሮፓውያኑ 2019 […]
ኢትዮጵያዊው አትሌት ዴሬሳ ገለታ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደ ማራቶን አሸንፏል !
የቤጂንግ ማራቶን እሁድ በቻይና ዋና ከተማ ተካሂዷል። በወንዶች ኢትዮጵያዊው ዴሬሳ ገለታ 2 ሰአት ከ7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ስያታጠናቅቅ በውድድሩ በዴሬሳ በአጨራረስ ተበልጦ ሁለተኛ የወጣው የሀገሩ ልጅ ይሁንልኝ አዳነ ሲሆን የኬኒያ አትሌት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ኬንያዊቷ ሺላ ቼፕኪሩይ በሴቶች በተመሳሳይ መልኩ የሩጫ ሰዓቱን 2 ሰአት ከ21 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ዘግታ አጠናቅቃለች። 2023 BEIJING MARATHON Men […]
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከ Nike ወደ ቻይናው ታላቅ ኩባንያ አንታ ስፖንሰሩ ዞሯል!
ኩባንያው የረጅም ርቀት ሯጮች ማሰልጠኛ በአፍሪካ እንደሚገነባ ይፋም አድርጓል! በ5000 ሜትር እና በ10,000 ሜትሮች ውድድሮች የአለም ክብረ ወሰን እና የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ባለቤትና የረጅም ርቀት ሯጩ አሁን ላይ ከዓለማችን ሦስት ፈጣን የማራቶን ሰዓት ካላቸው አንዱ የሆነው ኡትዮዽያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከስፖንሰሩ ከNike ኩባንያ ጋር ያለውን ውል ተቋጭቶ ከቻይናው ኩባኒያ አንታ ጋር መስማማቱን ተሰምቷል። እ.ኤ.አ […]
ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሊና ሜየር በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ በመሆን አዲስ አበባ ትገባለች!
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህዳር ዘጠኝ በሚከናወነው 23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10ኪሜ ኢንተርናሽናል ውድድር የ1992ቱ ባርሴሎና ኦሊምፒክ የ10,000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊዋ ኤሊና ሜየር በክብር እንግድነት እንደምትገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት በተለይም በውድድሩ የመጨረሻ ዙሮች ከኢትዮጵያዊቷ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ ጋር ባደረገችው ጠንካራ ፉክክር እና ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ ከደራርቱ […]
South Africa’s Elana Meyer will travel to Addis Ababa as VIP guest for the 2023 GER International 10k race
Great Ethiopian Run has announced that one of South Africa’s most celebrated distance athletes Elana Meyer will come to the race as a VIP guest. Meyer is best remembered for her epic duel with Ethiopia’s Derartu Tulu in the 1992 Barcelona Olympics 10,000m where she won the silver medal behind Tulu. Meyer also won the […]