አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ በተደረገ የሴቶች 800 ሜትር አትሌት ጽጌ ዱጉማ ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች። አትሌት ጽጌ ርቀቱን 1 ደቂቃ 56 ሰከንድ ከ64 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈችው፡፡
አትሌቲክስ
በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው የወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ አሸንፏል፡፡ አትሌቱ ርቀቱን በ12 ደቂቃ 50 ሰከንድ ከ45 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ ሌላኞቹ ኢትዮጵያውያን አትሌት ኩማ ግርማ እና አትሌት መዝገቡ ስሜ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ በተመሳሳይ በሻንጋይ በተደረገ የወንዶች […]
በሴቶች የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች!
በ45ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡ አትሌት ትግስት ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሠከንድ ፈጅቶባታል፡፡ በዚሁ ውድድር መርሐ-ግብር ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ የለንደን ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው ከዓለም ትላልቅ ማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ነው፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ አትሌት መሰረት ደፋርን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ!
28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡ የሚታወስ ነው። በጉባኤው የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ። በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ […]
አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ
አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም ከኦሮሚያ ክልል የተወከለው አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጧል፡፡
የወላይታ ድቻ ወሳኝ ተጨዋቹ ወደ ግብጽ ሲጓዝ ዛሬ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል!
በተጠናቀቀው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው እና በዘንድሮ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ላይ የዋንጫ ፍልሚያ ላይ የደረሰው የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ጀምሯል. በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ወላይታ ድቻ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጎልቶ የወጣውን አጥቂ ቢንያም ፍቅሬ በግብፅ ክለቦች ተፈልጎ በአሁን ሰአት ካይሮ እንደሚገኝ ሲታወቅ ተጨዋቹ በግብፁ እስማኤሊያ አልያም የቀድሞ […]
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ !
ኢኤስፒኤን (ESPN) የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል። ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደረጃ […]
በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ይፋ ሆነዋል!
በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ማራቶን በሴቶችና በወንዶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣አትሌት አማኔ በሪሶ፣አትሌት መገርቱ ዓለሙ፣አትሌት ጎይቶቶም ገ/ስላሴ (ተጠባባቂ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣አትሌት ሲሳይ ለማ፣አትሌት ዴሬሳ ገለታ፣ አትሌት ታምራት ቶላ (ተጠባባቂ) 800 ሜትር በሴቶች አትሌት ፅጌ ድጉማ፣አትሌት ሐብታም ዓለሙ፣አትሌት ወርቅነሽ መለሰ፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው […]
በ23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አግኝታለች !
በካሜሩን ዱዋላ ዛሬ በተጀመረው 23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ እና አትሌት ውብርስት አስቻለ ተከታትለው በመግባት ለሀገራቸው የወርቅና የብር ሜዳሊያ አምጥተዋል።
ኢትዮጵያውያን በፓሪስ ኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች በስፔን ነርጃ ምሽቱን ድንቅ ብቃት አሳይተዋል!
ወጣት አትሌት ቢኒያም የአለም ከ20 አመት በታች ክብረወሰንን ሰበሯል ! ኢትዮጵያን በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች መምረጫ በስፔን ነርጃ ምሽቱን በተካደው የ10,000 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል። ውድድሩን ፎትዬን ተስፋይ በ29፡47.71 በቀዳሚነት ስታሸንፍ ,ፅጌ ገብረሰላማ በ29፡49.33 እና እጅጋየሁ ታዬ 29፡50.52 ሁለተኛ እና ሶስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል። በተመሣሣይ በወንዶች የ10,000 ሜትር ውድድር […]