የስፖርት ዞን የታሪክ አሻጋሪ የሆኑ ግለሰቦችን እውቅና ሲሰጥ ስድስት ግለሰቦችን ተሸላሚዎች አድርጓል። በዚህም መሰረት :- በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ የባህል እና ስፖርት ሚንስተር አቶ መስፍን ቸርነት ፣ የፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ጨምሮ የስፖርቱ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። በመጀመሪያው የሽልማት ስነ-ስርዓት የአፍሪካን የነፃነት እግር ኳስ ያጀቡ አፓርታይድን በስፖርቱ የተዋጉት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የታሪክ አሻጋሪ […]
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ
“ከወልቂጤ ከተማ ጋር ረጅም እና ስኬታማ መንገድን አስባለሁ” ➖ጫላ ተሺታ (ወልቂጤ ከተማ)
በደረጃ ሰንጠረዡ በስድስተኛ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በ18ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ከባህርዳር አቻነው በ2 ለ2 አቻ ውጤት ተለያይተዋል። በወልቂጤ በኩል ጎል ካስቆጠሩት እና ድንቅ ብቃት ላይ ከሚገኙ ተጨዋች አንዱ ወጣቱ ጫላ ተሺታ ለሁለተኛ ጊዜ የጨዋታው ምርጥ ተጨዋቾች ተብሏል።ጫላ ተሺታ ከጨዋታው በኋላ አጭር ቆይታ አድርጓል። –-ስለጨዋታው ሲናገር… ” ጨዋታው ትንሸ ከበድ ይላል። እነሱ ከሽንፈት ነበር […]
የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎች!
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ የሚያደርገውን የስድስት ሳምንት ጨዋታዎች ቆይታ ካሳለፍነው አርብ መጀመሩ ይታወቃል ። ከዚሁ ቀን ጀምሮም ለተከታታይ አራት ቀናት የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው በነዚህ 8 ጨዋታዎች 30 የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርዶችን ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች የተመለከቱ ሲሆን ምንም አይነት የቀይ ካርድ አልታየም ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 […]
የ9ኛ ሳምንት ቤትኪንግ መጠናቀቅ በኋላ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተሰጥተዋል!
ለ9 ሳምንታት በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ሲባል ተቋርጧል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ታህሳስ 16 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ በዲስፕሊን መመሪያው መሰረት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በ9ኛ ሳምንት የተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ሁሉም […]
“በቀጣይ ጨዋታዎችም በዚሁ የሊጉ የመሪነቱን ይዘን እንቀጥላለን “— ዋና አሰልጣኝ ስዪም ከበደ
የ2013 ዓ.ም የኢትዮዽያ ፕሪምየር ቻምፒይና የነበረው እና አሁን ስምንተኛ ሳምንት ባስቆጠረው የ2014: ፕሪሚየር ሊግ በመሪነት ላይ የሚገኘው የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን ፋሲል ከነማ እስካሁን ባደረጋቸው 7 ጨዋታዎች በ14 ነጥብ የሊጉን መሪነት ይዞ ሲገኝ ሁለተኛ ደረጃ የሚከተለው ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻን በአንድ ነጥብ በልጦ እየመራ ይገኛል። የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ዛሬ በ12 : 00 […]
– የ2014 የውድድር ዓመቱን ባለሜዳዎቹ በድል ጀምረዋል! – ዳዊት የመጀመሪያው ቀይ ካርድ
የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 7 – ታህሳስ 15 ድረስ የመጀመሪያው ዙር ውድድር በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ ላይ የሚካሄድ ይሆናል። በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ቀናት በሚካሄደው የ2014 ውድድር የመክፈቻ ጨዋታው በሜዳው ባለቤት አሸናፊነት ተጠናቋል። በመጀመሪያውን ቀን የ2014 ቤትኪንግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ በ10 ቁጥሩ በመስፍን ታፈሰ ብቸኛ ጎል ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 […]
ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጀሪያ ሊያመራ ነው ! ጌታነህ ወደ ፋሲል ከነማ?
የ2013 ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ከጎል አዳኛቸው ሊለያዪ ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጄሪያው Jeunesse Sportive de Kabylie Fc (JSK) ሊያመራ መሆኑ ተሰምቷል ። ኢትዮኪክ ጉዳዮን ከሰማንበት ጊዜም ጀምሮ ስለጉዳዩ ሙጂብ ቃሲምን ጠይቀን ምላሹን እየጠበቅን ሲሆን ሙጂብን እንዳገኘነው ምላሹን የምናሠማ ይሆናል። እንደ መረጃው ከሆነ ግን የሙጂብ የአልጄሪያው ዝውውር መሣካቱ ተሰምቷል። በተጨማሪም የፋሲል ከነማ አመራሮች ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ […]
ኦኪኪ አፎላቪ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን አኑሯል
የ2013 ዓ.ም ሻምፒዮና የነበረው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾች ውል ያደሰ ሲሆን ወሳኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በዚህ መሠረት ከሀገሩ ናይጀሪያ ሆኖ የቅድመ ስምምነት የፈረመው ኦኪኪ አፎላቪ በዛሬው እለት ኢትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ለአንድ አመት የሚያቆየውን ውል ከዓፄዎቹ ጋር ፈርሟል ።
የኢትዮጵያ ቡና ለኮንፌዴሬሽንና ለቀጣይ ዓመት ዝግጅት ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል !
ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እና ለ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዝግጅት እንዲረው የኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል፡፡ ለአንድ ወር በቢሾፍቱ ከተማ በሚያደርገው ቆይታ ልምምዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሜዳ አድርጎ ማረፊያውን በኪሎሌ ሆቴል እንደሚያደርግ የክለቡ መረጃ ያመለክታል። በቡድኑ የአሰልጣኞች ስታፉ እንዲሁም ከወጣት ቡድኑ እና ዋናው ቡድን 35 ተጫዋቾች በዝግጅቱ መካተታቸው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ መረጃ ያመላክታል።
– ሳልሀዲን ሰይድ ከ14 ዓመት ቆይታ በኃላ ከፈረሰኞቹ መለያየቱ እርግጥ ሆነ !
በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት በ7 ቁጥር መለያው በአጥቂው ቦታ ተወዳጁ ተጨዋች የነበረው ሳልሀዲን ሰኢድ ከፈረሰኞቹ ሊለያይ መሆኑን ኢትዮኪክ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። ተወዳጁ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምበል ሳልሀዲን ሰኢድ በ1999 ዓ.ም ልክ እንዳሁኑ በክረምት የዝውውር ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድንን የተቀላቀለው። በቅዱስ ጊዮርጊስ እያለ ለሶስት ዓመታት በግብፅ ሊግ የመጫወቱ ዕድል አግኝቷል። በኃላም ተመልሶ […]