ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ በአርባ ምንጭ ይፈፀማል! በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን፤ በቁርባን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ። ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት […]
ዜናዎች
የፊታችን ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ ለሚካሄደው በ45ኛው ዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የሚካፈለው የልዑካን ቡድን ዛሬ በቤለቪው ሆቴል ተሸኘ :: በመርሀግብሩ መጀመሪያ የቡድኑ መሪና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ተስፋዬ አስግዶም ስለቡድኑ አጠቃላይ ቆይታቸው የወሰዱት የአካል እና የስነልቦና ስልጠና ለውጤታማነት እንደሚያበቃቸው በመተማመን መልካም እድል ለቡድኑ ተመኝተዋል ። አትሌቶችን በመወከል ደሞ አትሌት ለምለም […]
አረንጓዴው ጎርፍ በአክራ ሰማይ ስር ተከታለው በመግባት አሸንፈዋል !
በጋና አክራ የ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተዋል በ5000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታለው ገብተዋል መዲና ኢሳ ብርቱካን ሞላ መልክናት ውዱ በወንዶች የ3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ለሃገራችን የወርቅ ሜዳልያ በአትሌት ሳሙኤል ፍሬው ተገኝቷል ሳሙኤል ፍሬው 8:24.30 ወርቅ 4ኛ አብርሃም ስሜ 8:27.30 5ኛ ሚልኬሳ ፍቃዱ 8:27.55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ጀምሯል!
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ለ26 ተጫዋቾች በትናንትናው ዕለት ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቾቹም በዛሬው ዕለት በመሰባሰብ ከቀትር በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ማከናወን ችለዋል። ኢትዮጵያ እና ሌሶቶ ሁለት ጨዋታዎችን የሚያከናወኑ ሲሆን ጨዋታዎቹም መጋቢት 12 እና መጋቢት 15/2016 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል። @EFF
ብሔራዊ ቡድኑ ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐሙስ መጋቢት 12 እና እሁድ መጋቢት 15 ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እስከ ነገ 6፡00 በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል። ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች ሰዒድ ሀብታሙ – አዳማ ከተማ ፍሬው ጌታሁን […]
የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሰባተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
🕳ድሬዳዋ ከተማ ክለብ ደጋፊዎች ድንጋይ ወደ ሜዳ ስለመወርወራቸው ሪፖርት ቀርቦ ሃያ አምስት ሺህ እንዲከፍል ተወስኗል! 👇 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ መጋቢት 02 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስቱ በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት […]
ፋሲል ከነማ የወዳጅነት ጨዋታ ከእስራኤል ክለብ ግብዣ ቀረበለት!
የቅ/ጊዮርጊስ እና የቡና ሁለት ተጨዋቾች በድብይ ክለብ የሙከራ ዕድል አግኝተዋል የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ የውድድር ዓመቱን ከመጀመራቸው በፊት በ2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ የብሔራዊ ቡድኑ አብዛኞቹን ተጨዋቾችን በማስፈረም ቀዳሚ መሆናቸው ይታወሳል። ፋሲል ከነማዎች የውድድር ዓመቱን በድል ከጀመሩ በኋላም በአንደኛው ዙር በ15 ጨዋታዎች ስድስት አሸንፈው በአምስቱ አቻ ወጥተው በአራቱ ደግሞ ሽንፈን […]
የጋና እና የኢትዮጵያ የምሽቱ ጨዋታ በጋና አሸናፊነት ተጠናቋል!
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በጋና አስተናጋጅነት ዛሬ በተጀመረው በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ ዛሬ ምሽቱን የምድቡን የመጀመሪያውን ጨዋታውን አድርጎ ተሸንፏል። በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ እየተመራ ወደ ጋና ያቀናው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከ 11 ቀሚ ተሰላፊዎች ጋራ አራት ተቀያሪ ተጨዋቾች ብቻ ይዞ ነው የተጓዘው። የጋና እና የኢትዮጵያ ቡድኖች በምሽቱ ጨዋታ ላይ መብራት በኬፕ […]
ኢትዮጵያ ከዓለም በ5ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች !
በስኮትላንድ ግላስኮው የ19ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም በ5ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች። 2 ወርቅ 1 ብር 1 ነሐስ
የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ የምሽቱ ተጠባቂ የፍፄሜ ውድድር!
በስኮትላንድ ግላስኮው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተወዳደሩበት የማጣርያ ውድድር ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ይታወሳል። በዛሬው ውጤት በ800ሜ የሴቶች ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ሀብታም አለሙ እና ፅጌ ዱጉማ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። የዛሬ ምሽቱ ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድር ምሽት 5:15 ሰዓት የሴቶች 3000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ድንቅ አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሂሩት […]