በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ የገቡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የማስፋፊያ ግንባታ እና መጫወቻ ሜዳውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፊራንኦል ቡልቻ የፌዴሬሽኑ ኘሬዝዳንት የተቀብሏቸው ሲሆን የስታዲየሙ ያለበትን ደረጃ ገለፃ አድርገውላቸዋል። በጎብኝታቸው የስታዲየሙን የተጫዋቾች መቀየሪያ የተገጠመውን እጅግ ዘመናዊ መቀመጫ ወንበሮቹ ተመልክተዋል። በዚህ የመስክ ምልከታ ላይ ኮሚሽነር […]
ዜናዎች
በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው ጨዋታ ሰኞ እንደሚካሄድ የሊጉ ኮሚቴ አሳውቋል
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባህር ዳር ከተማን ከወልቂጤ ከተማ የሚያገናኘው የጨዋታ መርሃ ግብር – የ2015 የሊጉ ኮከብ ተጫዋቾች እጩ፣ የኢትዬጵያ ቡሔራዊ ቡድን እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ይታወቃል። ይህ የተራዘመው መርሃ ግብርም ሰኞ ሚያዝያ 14/2015 በ12:00 ሰዓት በድሬደዋ ስታዲየም እንደሚካሄድ […]
ኢትዮጵያ የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በሁለተኝነት አጠናቀቀች!
በቤለግሬድ 2024 የ45ኛውን የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ ኪሎ ሜትር ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣6 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡ በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን […]
የፋሲሉ አማኑኤል በትላንቱ ግጭት ላልተወሰነ ጊዜ ከእግርኩዋስ እንደሚርቅ አሰልጣኙ ተናግረዋል!
ትላንት የ19ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ የፋሲሉ ከነማው የአጥቂ መስመር ተጨዋች አማኑኤል ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል። የክለቡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስለ አማኑኤል ገብረሚካኤል የትላንት ምሽቱን ጉዳት አስመልክተው በማህበራዊ ገፃቸው ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ። ” ጥቃቅን የሚመስሉ ጉዳቶች የጭካኔ ታክሎች ብዙዎችን ከህልማቸው አሰናክለዋል:: ለዚህ ከባድ ጥፋት ክእግዜር ቀጥሎ […]
የጨዋታ ማራዘም መረጃ!
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባህር ዳር ከተማን ከወልቂጤ ከተማ ያገናኛል። ነገር ግን የ2015 የሊጉ እጩ ኮከብ ተጫዋች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰን ጊዜ መራዘሙን እየገለፅን በቀጣይ የሚወሰነውን የመጫወቻ መርሃ ግብር የምንገልፅ ይሆናል። የኢትዮጵያ […]
የአለልኝ አዘነን 23 ቁጥር ማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ ክለቡ ወሰነ !
በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ አስታወቀ። የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ ስፍራው በመገኘት ገልፀዋል። በዚህም አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰው የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብሰው ሆኖ በክብር […]
አዲሱ ሙሽራ አለልኝ አዘነ ከዚህ አለም በድንገት ማለፉ – ጥልቅ ሀዘን !
ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ በአርባ ምንጭ ይፈፀማል! በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን፤ በቁርባን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ። ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት […]
የፊታችን ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ ለሚካሄደው በ45ኛው ዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የሚካፈለው የልዑካን ቡድን ዛሬ በቤለቪው ሆቴል ተሸኘ :: በመርሀግብሩ መጀመሪያ የቡድኑ መሪና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ተስፋዬ አስግዶም ስለቡድኑ አጠቃላይ ቆይታቸው የወሰዱት የአካል እና የስነልቦና ስልጠና ለውጤታማነት እንደሚያበቃቸው በመተማመን መልካም እድል ለቡድኑ ተመኝተዋል ። አትሌቶችን በመወከል ደሞ አትሌት ለምለም […]
አረንጓዴው ጎርፍ በአክራ ሰማይ ስር ተከታለው በመግባት አሸንፈዋል !
በጋና አክራ የ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተዋል በ5000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታለው ገብተዋል መዲና ኢሳ ብርቱካን ሞላ መልክናት ውዱ በወንዶች የ3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ለሃገራችን የወርቅ ሜዳልያ በአትሌት ሳሙኤል ፍሬው ተገኝቷል ሳሙኤል ፍሬው 8:24.30 ወርቅ 4ኛ አብርሃም ስሜ 8:27.30 5ኛ ሚልኬሳ ፍቃዱ 8:27.55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ጀምሯል!
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ለ26 ተጫዋቾች በትናንትናው ዕለት ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቾቹም በዛሬው ዕለት በመሰባሰብ ከቀትር በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ማከናወን ችለዋል። ኢትዮጵያ እና ሌሶቶ ሁለት ጨዋታዎችን የሚያከናወኑ ሲሆን ጨዋታዎቹም መጋቢት 12 እና መጋቢት 15/2016 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል። @EFF