🔔- ሀጎስ የኢትዮጵያን ሪከርድ ሰብሯል ! በኦስሎ የምሽቱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደናቂ ብቃት አሳይተዋል። ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ሀጎስ ገብረሕይወት በ5000ሜ. 12፡36.73 በሆነ ሰአት፣በታሪክ ሁለተኛ ፈጣን ሆኖ ሲያሸንፍ በኢትዮጵያ አዲስ ክብረወሰን ሆኖ አጠናቋል። በ5ሺ ህ ሜትር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 12 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ ይዞት የነበረውን የኢትዮጵያ ክብረወሰን ነው አትሌት […]
ዜናዎች
🛑 የአዲሱ የብሔራዊ ቡድኑ ብራንድ ጥያቄ እያስነሳ ነው!
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ አዲስ የትጥቅ ብራንድ ቱርክ ከሚገኝ የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር በመተባበር “ሀገሬ” የተሰኘ የራሱን ብራንድ ስምምነት ላምበረት አካባቢ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ዛሬ ማስተዋወቁ ተገልጿል፡፡ እንደ መረጃዎች አዲሱ ብራንድ የተለያዪ ጥያቄዎች እያስነሳ ሲሆን በተለይም ፌዴሬሽኑ ከተቋሙ ጋር የመግዛት እና የመሸጥ ስምምነት የጊዜ ገደብ አለማድረጉ በተለያየ መልኩ ጥያቄን አስነስቷል. […]
-ዋልያዎቹ ዝግጅት ጀምረዋል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ልምምድ በማከናወን ጀምሯል።
🛑ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን ነገ ይጀምራሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ለሚያደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች የሚያደርገውን ዝግጅት በመጪው ሰኞ ይጀምራል ። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ሰኞ ከ4:00 ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ተላልፏል።
ድሪቤ ወልቴጂ አሸንፋለች !
አትሌት ድሪቤ ወልቴጂ እየተካሄደ ባለው ዳይመንድ ሊግ 💎DL in Eugene🇺🇸 በሴቶች 1500ሜ ርቀቱን በአስደናቂ ብቃት 3፡53.75 አሸንፋለች .
💎 በሴቶች 5,000 ሜትር የዳይመንት ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል!
በምሽቱ የዳይመንት ሊግ ውድድር # DL Prefontaine Classic Eugene🇺🇸 በ5.000 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያን አትሌቶች ከ 1ኛ – 6ኛ በአስደናቂ ውጤት አሸንፈዋል. ውድድሩን በቀዳሚነት በምርጥ ሰዐት 🥇#Tsigie_GEBRESELAMA🇪🇹 14፡18.76 ደቂቃ ስታሸንፍ እሷን ተከትለው እስከ ስድስተኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል. በውድድሩ በ5ኛነት ያጠናቀቀችው ታዳጊ #Birke HAYLOM 🇪🇹 ከ20አመት በታች በ14፡23.71 አዲስ ሪኮርድ አስመዝግባለች. በትውልደ ኢትዮጵያዊት ዜግነቷ ሆላንዳዊቷ የሆነችው አትሌት […]
በምሽቱ የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የዳይመንት ሊግ በሚያስቆጭ መልኩ ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት የአለም ክብረወሰኑን ተረከበች !
🛑በምሽቱ የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የዳይመንት ሊግ በሚያስቆጭ መልኩ ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት የአለም ክብረወሰኑን ተረከበች ! 👇 በምሽቱ የዳይመንት ሊግ ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት የ10ሺህ ሜትር የአለም ክብረ ወሰንን በሚያስቆጭ መልኩ (28:54.14) ከ29 ደቂቃ በታች በሆነ ጊዜ በመግባት በለተሰበት ግዳይ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰ መውሰድ ችላለች. የ5ኪሎ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት ጉዳፍ […]
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መረጃ !
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ23ኛ እስከ 26ኛ ሳምንት በሀዋሳ ከተማ – ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት የሊጉ 27ኛ ሳምንት ቀድሞ በወጣለት መርሃ ግብር የማይካሄድ መሆኑን እየገለፅን ከብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታ መልስ በቀጣይ በሚገለፅ መርሃ ግብር ሊጉ የሚቀጥል ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ
የብሔራዊ ቡድኑ የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል!
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም ወደ መጨረሻው የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል። በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታቸውን ከኬንያ ጋር በናይሮቢ ኡሊንዚ ስፖርትስ ኮምፕሌክስ ያደረገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኬንያ 3-0 ተሸንፎ የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል።
ባንኮች በሰፋ የጎል ልዩነት አሸንፈው የሊጉ መሪነት አጠናክረዋል!
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ# Week 25 ወላይታ ድቻ 0 – 5 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 20′ ፍፁም ግርማ(በራስ ላይ) 28′ ባሲሩ ዑማር 44′ ሳይሞን ፒተር 55′ ኤፍሬም ታምራት 77′ ኪቲካ ጅማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሐሙስ ግንቦት 08/