ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድንቅ አጥቂ ከፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ በቴላቪብ ተወያዩ !

ከእስራኤል ብሔራዊ ቡድን ይልቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቱን ከዚህ ቀደም በተደጋገሚ ለኢትዮ ኪክ የገለፀው እና በዘንድሮ የእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ሳልልህ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ከፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነ መልካም ውይይት ዛሬ በቴላቪቭ አደረጉ። ለረጅም ዓመታት ሲጠበቅ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የመጨረሻውን ዕድል ተጠቅመን ወልቂጤ ከተማን በሊጉ ለማቆየት የተቻለንን ሁሉ መሠዋት እናደርጋለን”- አቡበከር ሳኒ

  የወልቂጤ ከነማ በዘንድሮው ቤትኪንግ ጅማሮ ላይ የተሻለ የእግር ኳስ እና በጥሩ ውጤት ዓመቱ ያጠናቅቃል ተብሎ የተገመተ ቡድን ነበር። በአንፃሩ የኮቫድ ወረርሽኝ ምክንያት ቡድኑ በውስጡ ይዟቸውን የነበሩትን ድንቅ ብቃት የነበራቸው ተጨዋቾች እስከመጨረሻው ማሳየት ሳይችል ክለቡ ከወራጅ ቡድን አንዱም ሆኖል። በቡድኑ የግል ብቃታቸው የተሸሉ እንቅስቃሴ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ደግሞ አቡበከር ሳኒ ነው።እንደሚታወቀው  በ2013 የኢትዮጵያ የቤት ኪንግ […]

ዜናዎች

የሴካፋው ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ሳምንት ወደ ባህርዳር ያቀናል ! – 7 ተጨዋቾች ዛሬ ተቀንሰዋል – ተጨማሪም ጠርተዋል

የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮጵያ ሊጀመር ሳምንታት ቀርተውታል። ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ሻምፒዮና    ከሰኔ 26/2013 ተጀምሮ እስከ ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑን በተመለከተ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ35 ተጫዋቾች […]

ዜናዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የልዑካን ቡድን ነገ ወደ እስራኤል ያመራል! – ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ታስቧል !

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሚመራውና ፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የያዘው የልዑካን ቡድን ነገ ወደ እስራኤል እንደሚጓዙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በኢትዮጵያ እና በእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች መካከል ከረጅም ወራቶች በፊት ታስቦ በኮሮና ምክንያት ሳይሳካ የቀረው የሁለቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የትብብር ስምምነቶችን በይፋ የማሳካት ሂደት እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ […]

ዜናዎች

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የቫር ዳኝነቱን ይመሩታል !

  የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሞሮኮው ግዙፍ ቡድን ዊድዳድ ካዛብላንካ እና በደቡብ አፍሪካው ካይዘር ቺፍ መካከል የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ነገ ሰኔ 12 እና በቀጣይ ሳምንት ሰኔ 19 ያደርጋሉ።ሁለቱ ቡድኖች በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የነገውን የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ጨዋታቸውን በሞሮኮ ስታዲየም የሚካሄዱ ሲሆን ሴኔጋላዊው ማጉቴ ንዲያዬ በመሀል ዳኝነት እና ከጋምቢያው ባካሪ ፓፓ ጋሳማ ደግሞ በቫር […]

ዜናዎች

የአዲስ አበባ ስታዲየምን እድሳት ለማድረግ የውል ስምምነት ዛሬ ተደረገ !

የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን የአዲስአበባ ስታዲየምን ለማሳደስ እና ኢንተርናሽናል ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ከተቋራጭ ድርጅቱ ጋር ዛሬ የውል ስምምነት አድርጓል ።እድሳቱ በቅድሚያ ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶች መሠረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን የመጫወቻ ሜዳው ፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች ፣ የተመልካች መፀዳጃ እና የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ስራዎችን ያካትታል ። የእድሳቱን ስራውን ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ ኃ.የተ. የግል ኩባንያ በ39,644,748.93 ብር የአሸነፈ […]

ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሴካፋው ሻምፒዮና ላይ ትውልደ ኢትዮጵያን ለማካተት የቡሩንዲን ታላቅ ተሞክሮ ዕውን ሊያደርጉ ነው!

የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ  ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾችን በተመለከተ ታላቅ እና ሲጠበቅ የነበረውን ሃሳብ ተግባራዊ ሊያደርጉ መሆኑ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካም ሆነ ከሌሎች ዓለማት በውጭ የሚገኙ […]

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ለአውሮፓ ታላቅ ክለብ ዛሬ ፊርማውን አኖረ!

የስዊዘርላድ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አባል የሆነውና የወደፊት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ በውሰት ሰጥቶት የነበረው የቀድሞ ክለቡ የስዊዘርላዱ ኒው ሻቴል ሙሉ ለሙሉ የራሱ በማድረግ የሁለት ዓመት ውል በዛሬው ዕለት አስፈርሞታል። ከኢትዮጵያዊያን ወላጆቹ ስዊዘርላንድ ውስጥ ተዎልዶ ያደገው ተስፈኛው ወጣት ማረን ሀይለስላሴ ከአደገበት ኤፍ ሴ ዙሪክ በተውሶ በ2019 ዓ.ም. ለግማሽ ዓመት በራፐርስቪል በኃላም ፣ በ2019/2020 […]

ዜናዎች

” ለአቡበከር ደቡብ አፍሪካ ቢመጣ ትልቁ ፈተና ባህሉና እንግሊዝኛ መናገር ችግር ይሆንበታል ፣ ጌታነህ የደረሰበትን ችግር እንደ ትምህርት መጠቀም አለበት”

  ኢትዮጵያዊው ድንቅ ልጅ አቡበከር ናስር በቀጣዩ የውድድር ዘመን በደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየርሺፕ እንዲጫወት ለማድረግ ከሶስት ያላነሱ የደቡብ አፍሪካ ክለቦች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የደቡብ አፍሪካዊ ኪክ ኦፍ ዶት ኮም ትላንት ዘግቧል። በ2013 የውድድር ዘመን በ 23 ጨዋታዎች 29 ግቦችን አስቆጥሮ የኢትዮጵያ የከፍተኛ የጎል ሪከሩዱን የሰበረው የ21 አመቱ አቡበከር ናስር ፈላጊዎች የበዙ ሲሆን ተጨዋቹ የአፍሪካ እና የአውሮፓ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

የሻምበል አበበ ቢቂላ የመታሰቢያ  የማራቶን ውድድር ዛሬ ንጋት ላይ ተካሄዷል ! – ኢትዮ-ኤሌትሪክ የቡደን አሸናፊ ሆኗል!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛ ፌዴሬሽን ዛሬ  ንጋት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ኮዬ ፈጬ አከባቢ የ37ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የመታሰቢያ  የማራቶን ውድድር አካሄዷል። በውጤቱም የሴቶች አሸናፊዎች 1ኛ በሸንቄ እሙሼ ከሲዳማ ፖሊስ 2:44:51 2ኛ ፋንቱ ኢቲቻ ከኦሮ/ውሃ ስራዎች 2:45:12 3ኛ ስንቄ ደሴ ከፌደ/ማረሚያ 2:45:14 4ኛ ሰላማዊት ጌትነት ከኢት/ኤሌትሪክ 2:45:55 5ኛ ብርሀን ምህረት ከኢት/ኤሌትሪክ 2:46:37 6ኛ ፅጌሬዳ ግርማ […]