ዜናዎች

– የሴካፋ አዘጋጅ ኢትዮጵያ ከሻምፒዮናው ውጪ ለመሆን ተቃርባለች! – የተሻለ ሁለተኛ ሆኖ ማለፉ ነገ ይታወቃል !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 10 እስከ 25/2013 ዓ.ም ድረስ በዘጠኝ የሴካፋ አባል አገራት መካከል በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ውድድር የምድቡ ሃላፊዎች እየተወቁ ይገኛል። ወደ ቀጣይ ዙር ኃላፊ የሚሆነውን ለማወቅ አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ ባደረጉት የምድብ ” ለ” የዛሬ ጨዋታ በ1 ለ 1 በአቻ በመጠናቀቁ ተከትሎ ቡሩንዲ በ4 […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

ቶኪዮ ከተጓዘው ከ100 በላይ የኦሎምፒክ ልዑካኑ ግማሹ ያህሉ ጥያቄ እያስነሳ ይገኛል!- አትሌቶች ተቀንሰው ለምን ልዑካኑ በዛ?

የ32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮሮና ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቶ ነገ በታዋቂው የጃፓን አርክቴክት ኬንጎ ኩማ በተሠራው ባለ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በፈጀው እና 68ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ያለ ተመልካች በሚደረግ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በይፋ ይጀመራል። በታሪካዊው እና ተጠባቂው የቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮዽያን ባንድራ በመከፈቻው ስነስርዓት ላይ ከፍ ለማድረግ ትላንት የተጓዘው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ከስድስት ሰአታት ቆይታ በኃላ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

-በቶኪዮ አየር ማረፊያ ለስድስት ሰዓታት ታግዶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኮቪድ ነፃ ሆነ !

ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣  ኮሮና ምክንያት ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ተዘግቦ ነበረ ፣ይሁንና አሁን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑካን ቡድን ከቶኪዮ አየር ማረፊያ ወጥቶ ወደ ተመደበለት ቦታ መግባቱን የቡድኑ መሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው  ገልጸዋል። ነገ በሚጀመረው 32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ […]

ዜናዎች

– ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የተሳተፈበት ጨዋታ በሜክሲኮ 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል !

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ  ከምትሳተፍባቸዉ የስፓርታዊ  ውድድሮች  በተጨማሪም  በእግር ኳስ ባለሙያም ተወክላለች። በቶክዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በእግር ኳስ ዳኝነት የወከለው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ረፋዱን የተደረገውን የወንዶች እግር ኳስ የምድብ ” ሀ ” ፈረንሳይ  ክ ሜክስኮ ጨዋታ በ4ኛ ዳኝነት መርቷል። ጨዋታውን በዋና ዳኝነት አውስትራሊያዊውያኑ ዋና ዳኛ ክሪስ ቤዝ እንዲሁም ፣ አንቶን ሽቼቲኒን ( 1ኛ […]

ዜናዎች

– የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና የነገው የኢትዮጵያ ጨዋታ የሰዓት ለውጥ ተደረገ !

በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ቀጣዮቹን የምድብ አላፊዎች የሚታወቁበት የቀሪዎቹ የሶስት ጨዋታዎች የጨዋታ መርሐ ግብር በኩል የሰዓት ለውጥ ተደረጓል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ መካከል የሚደረገው የነገ ጨዋታ በቅድሚያ 10:00 ሰአት እንዲደረግ መርሐ ግብር ወጥቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተሻሻለው የውድድር ሰዓት በ8:00 ሰአት የሚደረግ ይሆናል። በወድድሩ መርሐ ግብር […]

ዜናዎች

ፈረሰኞቹ የ64 ዓመቱን ስርቢያዊ አዲስ አሰልጣኝ አድርገዋል !

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን ይፋ አድርጓል። እንደ ክለቡ መረጃ አሰልጣኙ የ64ዓመቱ ስርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲች  ሲሆኑቀደም ሲል የስርቢያን ከ17 ዓመት በታች እና ከ19 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ ቡድኖችን በማስልጠን የካበተ ልምድ ያላቸው እንደሆኑ ክለቡ ግልዖ  አሰልጣኙ ካስለጠኑባቸው ክለባች መካከልም የሩዋንዳው ዜስኮ ዩናይትድ ፣ዲሞክራቲክ ኮንጎ ቲፒ ማዜንቤ ፣የደቡብ አፍሪካው ፖሎ ኪዊን ሲቲ […]

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ- በሊቨርፑል የመጀመሪያውን አዲስ  የኮንትራት ስምምነት አኖረ!

ከለምለሚቱ የኢትዮጵያ ምድር በከንባታ ጠንባሮ ተወልዶ ከታላቅ ወንድሙ መለሰ ጋር እድገቱን በጀርመን ያደረገው ትውልድ ኢትዮጵያዊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ በፈረንጆቹ 2020 ዓ/ም ከጀርመኑ ከሆፌንሄም የሊቨርፑልን አካዳሚ መቀላቀሉ ይታወሳል። የ 17 ዓመቱ ወጣት ባለፈው ክረምት ቀዮቹ የተቀላቀለ ሲሆን የውድድር ዘመኑን ከ 18 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር አሳልፏል ፡፡ መልካሙ ፍራንዶንዶፍ በሊቨርፑል “AXA” ማሠልጠኛ ማዕከል የ 2020/21 የውድድር ዘመን […]

ዜናዎች

– የሳምንቱ አንኳር የዝውውር መረጃዎች – ባህርዳር ከነማ አቡበከርን በከፍተኛ የወርሀዊ ደሞዝ አስፈረመ !

ባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን ከቀናት በፊት የቀጠረው ባህርዳር ከነማ የተጨዋቾች የዝውውር ሂደቶችን በይፋ ማስፈረም ቀጥለዋል። ዛሬ በተሰማው መረጃ የጅማ አባጅፋሩን ወጣት ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በከፍተኛ ወርሀዊ ፊርማ የጣና ሞገዶችን መቀላቀሉ ታውቋል። ሐዋሳ ከተማ በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን  የቀጠረው ሐዋሳ ከተማ የነባር ተጨዋቾችን ውል ማደስ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት የክለቡ ወሳኝ ተጨዋች የኤፍሬም […]

ዜናዎች

ኤርትራ በቡሩንዲ ሽንፈትን አስተናግዳለች!

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ በመክፈቻው ጨዋታ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በሦስት እኩል አቻ የጀመሩት የኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከቡሩንዲ አቻቸው ባደረገው ጨዋታ የ3 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል። በትላንቱ የከባድ ዝናብ ምከንያት የሁለተኛው አጋማሽ የተቋረጠው እና ዛሬ ረፋድ በቀጠለው ጨዋታ የቡሩንዲ ታዳጊ ቡድ ን በዛሬው ጨዋታ ሁለት […]

ዜናዎች

– ናትናኤል ከዓፄዎቹ ጋር የውል ስምምነቱን ለሶስት አመት አራዝሟል !

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ እና አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈርም ላይ ይገኛል። 2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት የሆነውና በካፍ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ  የናትናኤል ገብረጊዮርጊስ የውል ስምምነት ለሶስት አመት አራዝመዋል።  በ2013  በዓፄዎቹ  በርካታ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ለቡድኑ ወሳኝ ነጥቦችን ያበረከተው […]