ዜናዎች

-ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ወሳኙን የደረጃ ጨዋታ በዋና ዳኛነት ይመሩታል !

በዓለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ በዋና ዳኝነት እና በረዳት ዳኝነት በብቃት በመወጣት የሚታወቁት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ነገም በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ተጠባቂውን የደረጃ ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል ። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ሰሞኑን በዋና እና ረዳት ዳኝነት የመሩት ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዓርብ የኦሎምፒክ አዘጋጇ ጃፓን ከ ሜክሲኮ ለሶስተኝነት (ለነሀስ ሜዳሊያ) የሚያደርጉትን […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኦኪኪ አፎላቪ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን አኑሯል

የ2013 ዓ.ም ሻምፒዮና የነበረው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾች ውል ያደሰ ሲሆን ወሳኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በዚህ መሠረት ከሀገሩ ናይጀሪያ ሆኖ የቅድመ ስምምነት የፈረመው ኦኪኪ አፎላቪ በዛሬው እለት ኢትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ለአንድ አመት የሚያቆየውን ውል ከዓፄዎቹ ጋር ፈርሟል ።

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና ለኮንፌዴሬሽንና ለቀጣይ ዓመት ዝግጅት ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል !

ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እና ለ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዝግጅት እንዲረው የኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል፡፡ ለአንድ ወር በቢሾፍቱ ከተማ በሚያደርገው ቆይታ ልምምዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሜዳ አድርጎ ማረፊያውን በኪሎሌ ሆቴል እንደሚያደርግ የክለቡ መረጃ ያመለክታል። በቡድኑ የአሰልጣኞች ስታፉ እንዲሁም ከወጣት ቡድኑ እና ዋናው ቡድን 35 ተጫዋቾች በዝግጅቱ መካተታቸው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ መረጃ ያመላክታል።

አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ሀብታም በ800 ሜትር የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆናለች !

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 800 ሜትር ለፍፃሜው የበቃችው አትሌት ሀብታም አለሙ ፍፃሜውን በ 1:57.56 በስድስተኛ ደረጃ  ጨርሳለች ። አትሌት ሀብታም የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን ማስመዝገብም ችላለች። ርቀቱን በትውልድ ሱዳናዊት በዜግነት አሜሪካዊት የሆነችው የ19 ዓመቷ አቲንግ ሙ 1:55 .21 በሆነ  ምርጥ  ሰዓት አሻሽላ በቀዳሚነት አሸንፋለች።  ሀብታም አለሙ በ800 ሜትር ያሳየችው ጥረት በርቺ ልትባል ይገባል። አትሌት ሀብታም […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

– በ5ሺህ ወንዶች በቶኪዮ የሚገኘው ሙክታር በሰዎች ስሜታዊነት በዛሬው ውድድር አይሰለፍም ?

የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮዽያዊያን የሚሳተፉበት ውድድር ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 27/2013 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ይደረጋል።በዚህ ርቀት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከ1ኛ – 4ኛ ወጥተው ባመጡት ፈጣን ሰአት እንደሆነ ይታወቃል። በአንፃሩ በ5ሺህ ሜትር በተደጋጋሚ በአጨራረስ የሚታወቀውና በርቀቱ ስመጥር የሆነውን የዓለም ድንቅ አትሌት ሞህ ፋራን ጭምር ያሸነፈው ሙክታር እንድሪስ በሀገር ውስጥ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

– አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5 ሺ ሜትር ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል !

ትላንት ምሽቱን ወደ ቶኪዮ  ያመራው 4ኛዙር የኢትዮዽያ ልዑካን ቡድን ቶኪዮ በሰላም መድረሱ ታውቋል። በአራተኛ ዙር ትላንት የተጓዘው የወንዶች 5000 እና 1,500 ሜትር የያዘው የኦሎምፒክ ቡድን መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ለዑካን ወስጥ የነበረው እና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝርዝር ያልተካተተው ሙክታር እድሪስ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ጥረት ወደ 5 ሺ እንዲገባ ተደርጓል ። በዚህ መሠረት ውጤታማው ድንቅ አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5ሺህ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

“ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ የታላላቆቼን ምሩፅ ይፍጠር፣ሀይሌ ገብረ ስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለን ታሪክ በመድገሜ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ ” – አትሌት ሰለሞን ባረጋ

  በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት ከ13 ዓመት በኃላ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያሰገኘ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል። ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አፈትልኮ በመውጣት ርቀቱን በ27:ከ43.22 በሆነ ጊዜ በአስገራሚ መልኩ ማሸነፍ ችሏል። በውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ዮጋንዳውያኑ አትሌቶች […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

– ምድብ ሁለት አትሌት ጌትነት ዋለ

አትሌት ጌትነት ዋለ በቶኪዮ በኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ ሩጫን በልጅነቱ 4 ኪ.ሜ ወደ ትምህርት ቤቱ በመሮጥ የጀመረው አሁን ላይ በኦሎምፒክ መድረክ በውጤት ከሚጠበቁ አንዱ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ በ13 ዓመቱ ወደ ሩጫው ዓለም እንደገባ ሲነገር በወቅቱ በ 1500 ሜትር እና በ 3000 ሜትር ርቀቶች በክልል ሻምፒዮና ላይ ያሳየው ውጤት አሰልጣኝ ተሾመ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

በምድብ 1 : ተወዳዳሪ አትሌት ለሜቻ ግርማ

የዛሬ ሌሊት 3ሺ ሜትር የወንዶች መሠናክል ማጣሪያ ከሌሊቱ 9 :30 ሰዓት ይጀመራል . አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክ በዶሀ የአለም ሻንፒዮና ላይ የብር ሜዳሊያ ማግኘት የቻለ ወጣት አትሌት ነው። በቅርቡ በሞናኮ ተካሄዶ በነበረው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኬኒያዊያንን አሸንፎ የአመቱን ፈጣን ሰአት አስመዝግቦ ማሸነፉ ይታወሳል። አትሌቱ በአሁን ሰዓት በርቀቱ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው አትሌቶች አንዱ ነው። ምንም […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

– ሳልሀዲን ሰይድ ከ14 ዓመት ቆይታ በኃላ ከፈረሰኞቹ መለያየቱ እርግጥ ሆነ !

በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት በ7 ቁጥር መለያው በአጥቂው ቦታ ተወዳጁ ተጨዋች የነበረው ሳልሀዲን ሰኢድ ከፈረሰኞቹ ሊለያይ መሆኑን ኢትዮኪክ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። ተወዳጁ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምበል ሳልሀዲን ሰኢድ በ1999 ዓ.ም ልክ እንዳሁኑ በክረምት የዝውውር ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድንን የተቀላቀለው። በቅዱስ ጊዮርጊስ እያለ  ለሶስት ዓመታት በግብፅ ሊግ የመጫወቱ ዕድል አግኝቷል። በኃላም ተመልሶ […]