ዜናዎች

የሀምበሪቾ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በለቅሶ እና በአሳዛኝ የድረሱልኝ ጥሪ እየተማፀኑ ይገኛል !

የ2016 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ያሳለፍነው እሁድ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ውድድራቸውን በማጠናቀቅ አብዛኛዎች የሊጉ ቡድኖች ወደ መጡበት ከተማ እና ተጫዋቾች ሆነ አሰልጣኞች ወደ የቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሀምበርቾ ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም ይርጋ ጨፌ ቡና ያገለገሉበትን በውላቸው መሰረት ክፍያ ማግኘት እንዳልቻሉ እንዲሁም ችግረኛ ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ቀርቶ እየተረዱ እንደሚገኙ ተደጋጋሚ ጊዜ ትዕንግርት […]

ዜናዎች

🏆የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን የኢትዮጵያ- ቻምፒዮን ሆነዋል.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለ7ኛ ጊዜ የ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነዋል.              

ዜናዎች

ቻምፒዮኖቹ ከሐዋሳ – አዲስ አበባ

ከሀዋሳ በድል የተመለሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 ቻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከቦሌ አየር ማረፊያ በመነሳት በክፍት አውቶቡስ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ደስታውን ከደጋፊዎች ጋር ተጋርቶ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት የአሸናፊነቱን ዋንጫ በመያዝ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝቶ በዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዜናዎች

ከንቲባ አዳነች የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ ሆነው ተሹመዋል!

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሾሟቸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ”አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋትን በተለይም የእግር ኳስ ሜዳዎችንን በማየት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰጠኝ እውቅና እንዲሁም የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሃላፊነት ስለሰጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ” […]

ዜናዎች

ራምኬል ሎክ የደቡብ ሱዳኑን ኤል ሜሪክ ክለብ ፊርማውን አኑሯል!

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያሳለፈው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመስመር ተጫዋች ራምኬል ሎክ የደቡብ ሱዳኑን ኤል ሜሪክ ቤንቲዩ እግርኳስ ክለብ ጋር ለመሠጫወት ፊርማውን አኑሯል.

ዜናዎች

የአዲስ አበባ ስታድየም ወንበር በአንድ ጨዋታ ተሰባብሯል!

እንደሚታወሰው ለዓመታት የአዲስ አበባ ስታደየም ከእድሳት ጋር በተያያዘ ጨዋታዎች ሳያስተናግድ ተዘግቶ ዛሬ የኢትዮጵያ ዋንጫ ማስተናገዱ ይታወሳል. እናም የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በተቀመጡበት በኩል የአዲስአበባ ስታዲየም ከእድሳት በኋላ በደጋፊዎች ፊት የመጀመሪያ ጨዋታ ሲደረግ ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2ለ1 ካሸነፈ በኋላ የድቻ ደጋፊዎች በተቀመጡበት ይህ ተከስቷል ።

ዜናዎች

🏆ኢትዮጵያ ቡና የ2016 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል!

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል። የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዋሳዋ ጂኦፊሪ 2x በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለጦና ንቦቹ አበባየሁ ሀጂሶ አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ ቡና ለአመታት ተቋርጦ በዚህ አመት የጀመረውን የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ለስድስተኛ ጊዜ ማሳካት ችለዋል። ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን […]

English ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 የሊጕ ቻምፒዮን ሆነ! #CBE 2016 EPL CHAMPIONS #

Commercial Bank of Ethiopia -CBE # For winning their first ever Ethiopian premier league title # 2016 CHAMPIONS # የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የቻምፒዮነት ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት እውን ሆኗል. በተመሣሣይ በአንድ ነጥብ ልዩነት የቻምዩናነት ዕድል የነበረው መቻል የዛሬውን ጨዋታ ቢያሸንፍም ንግድ ባንክ አሸናፊ በመሆኑ በአንድ ነጥብ ተበልጦ የቻምዮናነት እልሙን ማሳካት ሳይችል ቀርቷል! የሙሉ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

⭕️ የዛሬው ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጨዋታ ውጤት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እጅ ላይ ነው ለሚለው አሰልጣኙ ምላሽ ሰጥተዋል!

የዛሬው ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጨዋታ ውጤት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እጅ ላይ ነው ለሚለው አሰልጣኙ ምላሽ ሰጥተዋል! “እንደዚህ አይነት አባባል መድንን አይመለከተውም ቀድሞ ያልተሰራ ነገር ከመድን ጋር ባለው ጨዋታ ሊሆን አይችልም “ – አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛው ሳምንት ሻምፒዮናውን የሚለይበት ተጠባቂ ጨዋታዎች በተመሣሣይ ሰአት ዛሬ ሰኔ 29 በ10: 00 ሰአት […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ይፋ ሆነዋል!

በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ማራቶን በሴቶችና በወንዶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣አትሌት አማኔ በሪሶ፣አትሌት መገርቱ ዓለሙ፣አትሌት ጎይቶቶም ገ/ስላሴ (ተጠባባቂ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣አትሌት ሲሳይ ለማ፣አትሌት ዴሬሳ ገለታ፣ አትሌት ታምራት ቶላ (ተጠባባቂ) 800 ሜትር በሴቶች አትሌት ፅጌ ድጉማ፣አትሌት ሐብታም ዓለሙ፣አትሌት ወርቅነሽ መለሰ፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው […]