ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎች!

  የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ የሚያደርገውን የስድስት ሳምንት ጨዋታዎች ቆይታ ካሳለፍነው አርብ መጀመሩ ይታወቃል ። ከዚሁ ቀን ጀምሮም ለተከታታይ አራት ቀናት የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው በነዚህ 8 ጨዋታዎች 30 የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርዶችን ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች የተመለከቱ ሲሆን ምንም አይነት የቀይ ካርድ አልታየም ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 […]

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወጣት አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋሮጦ የሰሜን አሜሪካውን ክለብ ተቀላቅሏል !

  በስዊዘርላንድ ዋናው ሱፐር ሊግ ለኤፍ ሲ ሉጋኖ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር እና ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ያለፉትን የውድድር ወራቶች አድናቆት ያተረፈው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ ቀጣዮን የፈረንጆቹ 2023 ወደ አሜሪካ በመጓዝ በአሜሪካ Major League Soccer (MLS) ለቺካጎ ፋየር ለመጫወት መስማማቱን ክለቡ በድህረ ገፁ ትላንት ይፋ አድርጓል። በፍጥነቱ እንዲሁም በተለየ የኳስ ጥበቡ የተለየ ችሎታ ያለው የ23 ዓመቱ […]

አፍሪካ ዜናዎች

➖የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በካሜሩኑ ውጤት የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀ !

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሩን ያሳየውን የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ፌዴሬሽኑ “ባቀድነው ልክ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ውጤታማ ባለመሆናችን የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን” የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል ። አቶ ባህሩ ቀጥለው “ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ […]

ዜናዎች

“እዚህ ትልቅ መድረክ ላይ በመመረጤ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል”-አማኑኤል ዮሐንስ

  የዋልያዎቹ የመሀል ሜዳው እስትንፋስ እና የመሀል ሜዳ ሞተሩ አማኑኤል ዮሐንስ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የጨዋታው ኮከብ በመባል ከካፍ ሽልማት ማግኘቱ ይታወሳል። አማኑኤል በካፍ ቴክኒካል ኮሚቴ በምድብ ጨዋታዎች ከምርጥ 11 ተጫዋቾች ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል በዕጩነት የቀረበ ብቸኛ ተጫዋች እንደነበር ይታወሳል። የዋልያዎቹ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማኑኤል ዮሃንስ ዛሬ ካፍ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በአፍሪካ […]

አፍሪካ ዜናዎች

“የነገው የመጀመርያ ጨዋታ ነው፣እነሱ ጠንካሮች ቢሆኑም እኛም የተሻለ ነገር ለማሳየት ዝግጁ ነን” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ጌታነህ ከበደ ነገ ምሽት 4፡00 ላይ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ከምታደርገው ጨዋታ ቀደም ብሎ ዛሬ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሀሳባቸውን በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች አካፍለዋል። ወደ ካሜሩን ለመድረስ የመጀመርያው ቡድን እንደሆንን በመግለፅ መግለጫቸውን የጀመሩት አሰልጣኝ ውበቱ ከሶስት አፍሪካ ዋንጫዎች በኋላ ወደ መድረኩ በመመለስ ጥሩ ቡድን ይዘው ለመቅረብ እና […]

አፍሪካ ዜናዎች

የኮቪድ ወረርሽኝ ዋልያዎቹ በሚገኙበት በምድብ 1 ሀገራት ላይ ጠንክሯል ! – ከዋልያዎቹ አራት ከካሜሩን አራት በኮቪድ ተይዘዋል !

የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ዘጠኝ ቀናት ብቻ ሲቀረው የውድድሩ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አስመልክቶ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች ከጨዋታው መጀመር በፊት ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። በተለይም ደግሞ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በተሳታፊ ሀገራት ላይ ሊደርስ የሚችለው የኮቪድ ጫና ሌላኛው ስጋት ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ነው። ከውድድሩ መጀመር በፊት ባለፈው እሁድ ከሀያ አራቱ ተሳታፊ ሀገራት ቀዳሚው ሆኗል ያውንዴ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]

አፍሪካ ዜናዎች

ፊፋ በወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ሲልቫይን ግቦሆ ላይ የዕገዳ ውሳኔ አሳልፏል !

የፊፋ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መልዕክት ሲልቫይን ግቦሆን በጊዜያዊነት እንዳገደ አስታውቋል።ለአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን እየተጫወተ የሚገኘው ሲልቫይን ግቦሆ በአሁኑ ወቅት በወልቂጤ ከተማ ተመዝግቦ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን ኖቬምበር ላይ አይቮሪኮስት ከጋቦን ጋር ስትጫወት በእጣ የዶፒንግ ምርመራ እንዲሰራለት ወጥቶበት የሽንት ናሙና ሰጥቶ ነበር። በዚህ ናሙና ውስጥም ትራይሜታዚዲን የሚባል ከ2014 ጀምሮ አትሌቶች እንዳይጠቀሙት በዋዳ የታገደ ንጥረ […]

አፍሪካ ዜናዎች

የዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ሱዳንን 3-2 አሸንፏል! – ቀጣይ ተጋጣሚያቸው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ካሜሩን ገብቷል

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ይረዳውዘንድ የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርጎ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት ጎሎችን ሽመልስ በቀለ አንድ ጎል በአጠቃላይ 3 ለ2 አሸንፏል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቻቸው በዛሬው ጨዋታ የቡድናቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም የቡድኑን ቀጣይ መሻሻል ያለበትን በተወሰነ መልኩ ያዪበት አጋጣሚ ነው ተብሎ ይገመታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]

ዜናዎች

ዋልያዎቹ የወዳጅነት ጨዋታ ነገ ከሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሩ በፊት  አቋሙን ለመፈተሽ ነገ የመጀመሪያ  የወዳጅነት ጨዋታውን  ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊው  አቶ ባህሩ ጥላሁን ባለፈው ሳምንት ቡድኑ ከአዲስ አበባ ከመነሳቱ በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዋልያውቹ  በካሜሩን የዝግጅት ጊዜያቸው ሁለት ወይም ሶስት   የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ማቀዳቸውን መናገራቸው ይታወሳል። በዚህ መሠረት ዋልያዎቹ […]

አፍሪካ ዜናዎች

#የዓለማችን 4ኛው ውድ ዋንጫ የአፍሪካ ዋንጫ ድዋላ ደርሷል !

በካሜሩን አዘጋጅነት በፈረንጆቹ ከJanuary 9 ተጀምሮ February 6 የሚጠናቀቀው የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር 10 ቀናት ቀርተዋል። አዘጋጇ ሀገር ካሜሩንም ውድድሩን ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ ለማካሄድ እንግዷቿን መቀበልም የጀመረች ሲሆን በካሜሩን የተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች በዓለማችን አምስተኛ ውዱ የሆነው የአፍሪካ ዋንጫም ለህዝብ በክፍት መኪና ለእይታ አየቀረበ ሲሆን አሁን ላይ ዋንጫው ከሊምቤ ወደ ሁለተኛ ዋና ከተማ ዱዋላ […]