አፍሪካ ዜናዎች

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጣይ ጊኒን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድኑ ከቻን ስህተቱ ለመማር በሚል የግምገማ መድረክ ዛሬ ተካሄዷል!

የኢትዮጵያ የቻን ብሔራዊ ቡድን በአልጄርያ አስተናጋጀነት በተከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ የልዑክ ቡድኑ አባላት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት ሐሙስ ጥር 25 በኢሊሊ ሆቴል ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ  የተባሉት ጉዳዮች የሚከተሉት ቢሆን ግምገማ  የተደረገው ሐሳብ   ከማውራት ባለፈ ለብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ  አሁን ላይ እረግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። […]

አፍሪካ ዜናዎች

#በነገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጎል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል። ሆኖም በአንጋፋው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በ 5፡00 ላይ የሚከናወን በመሆኑ የሰዓት መጣበብ እንዳይኖር በማሰብ ጋዜጣዊ መግለጫው […]

ዜናዎች

#እጅግ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ዜና ዕረፍት !

እጅግ ሲበዛ በጋዜጠኝነት ስፖርት ሳይታክትና ሳያርፍ እልፍ ዘመናትን ሲሰራ አሁንም በመስራት ላይ የነበረው ታሪክ አዋቂው ወንድማችን የጋዜኛ መሸሻ ወልዴ ትላንት ማምሻውን ህይወቱ ማለፉ ተዘግቧል። ኢትዮኪክ ለቤተሰቦቹ ለስራ ባልደረቦቹ እና ለሚያውቁት ሁሉ መፅናናትን እየተመኘን ፣የምናከብረው የወንድማችን የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ነፍስ ይማር እንላለን !

አፍሪካ ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የአልጄሪያ ቆይታቸው አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገትን አጭር ቆይታ እና ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ ይሰጣሉ።

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ፈረሰኞቹ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልምምድ ስፍራና ሆስቴል ግንባታ መሬት ባለቤትነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተረከቡ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም በወሰነው ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የልምምድና የተጫዋቾች ማረፊያ ሆስቴል ግንባታ ቦታ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፤ በመሆኑም ክለቡ አስፈላጊውን የሊዝ ውል በመፈፀም እና ለይዞታውም በ20/05/2012 ዓ.ም. ካርታ በማግኘት ጭምር ቦታውን ለማልማት የተለያዩ ጥረቶች ያደረገ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት ቆይቷል። በተለይም በይዞታው ላይ 3 የይገባኛል ክሶች ቀረበው ከሁለት ዓመታት […]

አፍሪካ ዜናዎች

የመጨረሻው የልዑካን ቡድን ዛሬ ሌሊት ይገባል

17 ተጫዋቾችን ጨምሮ 24 አባላትን በመያዝ ከአልጄርያ የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ በግብፅ ትራንዚት አድርጎ ከአራት ሰዓታት በረራ በኋላ ሌሊት አዲስ አበባ ገብቷል። በትናንትናው ዕለት 12 የብሔራዊ ቡድን አባላት ሀገር ቤት መድረሳቸው ይታወሳል። የመጨረሻው የልዑካን ቡድን ዛሬ ሌሊት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል     መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን :- https://www.instagram.com/ethio_kick ድረ ገጻችንን :- https://ethio-kickoff.com

ዜናዎች

# የሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት ዛሬ ይዘጋል!

የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ የ2015 ዓ.ም አጋማሽ የተጫዋቾች ዝውውር ከታህሳስ 18/2015 (December 27) ጀምሮ እስከ ጥር 18/2015 (January 26) ድረስ ለአንድ ወር ቆይቶ ዛሬ የሚዘጋ ይሆናል። በዘንድሮው የሁለተኛ ዙር የዝውውር እንቅስቃሴ ላይ ክለቦች ብዙም ተሳትፎ ያላደረጉበት ነበር ማለት ይቻላል ። በአንፃሩ የዝውውር መሥኮቱ ዛሬ በይፋ ከመዘጋቱ በፊት ተጨዋቾች ያስፈረሙና በስምምንት የተለያዩ ክለቦች ታይተዋል። #ፋሲል ከነማ […]

አፍሪካ ዜናዎች

አደይ አበባ ስታድየም በጊዜ ባለመጠናቀቁ ወጪው የ13.3 ቢሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል!

ከስድስት አመት በፊት የተጀመረው የአደይ አበባ ስታደየም ግንባታ ስታድየሙ ሲጀመር በ5.7 ቢሊየን ብር ለማጠናቀቅ ቢታሰብም አሁን ላይ ግንባታውን እየሰራ ያለው የቻይና መንግስታዊ ድርጅት 19 ቢሊየን ብር ጠይቋል። ግንባታው የተቋረጠው የአደይ አበባ ስታድየም እንዲጀመርም ውሳኔዎች ያስፈልጉታል። በአንድ ወር ግዜ ውስጥም መፍትሄ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ጋዜጠኛ ሀብታሙ ካሳዬ ዘግቧል #እኛ ከደረሱን መረጃዎች አንዱ ግንባታውን እያደረገ ያለው ካምፓኒ […]

አፍሪካ ዜናዎች

# የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ወደ አገሩ ዛሬ ለመመለስ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል!

#ከተሳካ ምናልባት ነገ ይደርሳሉ! በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ከጥር 5/2015 ጀምሮ እስከ ጥር 27/2015 ድረስ በሚቆየው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ከምድቡ ማለፍ ሳይችል በጊዜ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ወደ ሀገሩ ለመመለስ ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል። በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ላይ ከአንድ ጎል በላይ ማስቆጠር ሳይችል ውድድሩ ላይ በሶስት ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት በምድብ […]

አፍሪካ ዜናዎች

የዋልያዎቹ አለቃና እና አምበል ነገ ከአልጄሪያ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል!

” ጨዋታውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁ ነን “ -አሰልጣኝ ውበቱ አባተ “በአካል ብቃቱም ሆነ በአእምሮ ረገድ ተዘጋጅተናል “ -አምበሉ መስዑድ መሀመድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከአልጄርያ አቻው ጋር ካለበት ጨዋታ አስቀድሞ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ መስዑድ መሀመድ የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ምን ተባለ ? አስቀድመው ስለነገው ጨዋታ የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ […]